Logo
Nafikot Slim Billboard Desktop 1600x160

አቦል ቲቪ ዙረት እና ናፍቆት ድራማን ይዞልዎት መቷል!

ዜና
27 ሜይ 2021
ከነዚህ ድራማዎች ይሄን መጠበቅ ይችላሉ።

አቦል ቲቪ ሁለት አዳዲስ ድራማዎችን በሚቀጥለው ሳምንት ሊያቀርብልዎት ነው! ዙረት እና ናፍቆት ድራማ የተለያዩ ታሪካቸን ይዘው በታዋቂና ተወዳጅ ተዋንያኖች ሊቀርብልዎት ተዘጋጅተዋል። 

ስለነዚህ ድራማዎች ይበልጥ ማወቅ ይፈልጋሉ? እነዚህን ያንብቡ!

ስለ ዙረት

አንድ የወንጀል ድርጅት ከሃገሪትዋ በህግወጥ መንገድ ብዙ ብር ለማውጣት ይጥራሉ። ይሄንን ለማካሄድ ወደ ኢትዮጵያ የመጣውን የድርጅቱ መሪ ለመያዝ አንድ የፖሊስ ሰላይ እራሱን ሹፌር አስመስሎ ድርጅቱ ውስጥ ይገባል። ነገር ግን፣ ሰላዩ የልጅነት ፍቅኛው የመሪው እጮኛ መሆንዋን ሲረዳ፣ ተልእኮው ይወሳስባል። በዙሪያው ባሉት ሳይዘናጋ ስራውን መቀጠል የሚችል ይመስልዎታል? የልጅነት ፍቅሩስ ማን እንደሆነ የምታውቅ ይመስልዎታል? ይሄን ለማወቅ ዙረትን ግንቦት 23 ከምሽቱ 2:30 ይከታተሉ!

ዙረት እነዚህን ታዋቂ ተዋንያኖች ይዞ በቅርብ ቀን ይቀርባል፡

ኪዳን

ኪዳን የ38 አመት ፖሊስ ሲሆን በሹፍርና የወንጀል ድርጅት ውስጥ ለስለላ ገብቷል።

ምዕራፍ

በልጅነቷ ጠፍታ ከሀገር ውጪ ስትኖር በአደጋ ምክነያት የምስታወስ ችግር ይገጥማታል። በ34 አመቷ በውጪ ሀገር የተዋወቀችውን እጮኛዋን ለማግባት ወደ ኢትዮጵያ ትመለሳለች።

ሱራፌል

ለሰርግ አስመስሎ ወደ ኢትዮጵያ  በመምጣት በህገወጥ መንገድ የወንጀል ድርጅቱን ገንዘብ ለማስወጣት ይሞክራል። ይህ የ44 አመት ወንጀለኛ ከእጮኛው ምዕራፍ ስራውን ከግንኙነታቸው መጀመሪያው ጀምሮ ይደብቃታል።

ስለ ናፍቆት ድራማ 

ታሪኩ ስለ አንዲት ጎበዝ ዘፋኝ እና በልጅነቷ ወልዳ ካላአባት ስላሳደገችው ልጇ ቃላብ ነው። ቃላብ ከእናቱ ገላ ጋር ምንም ሳያጣ ያድጋል፣ የዘፈን ፍቅሯንም ይጋራል ግን እህት እና ወንድም በመፈለጉ ይጨቀጭቃታል። ስለዚህም ገላ ለአብቃል ብላ ሙዚቃ ፍቅር ያላቸው ሶስት ልጆች ከጉዲፈቻ ወስዳ አብራ ታሳድጋቸዋለች። እህቱን በማፍቀሩ ቃላብ ከእናቱ እና ወንድሙ ጋር ሲጣላ ከቤት ይጠፋል ግን ገላን በመታመሟ ያአብቃልን ማፈላለግ ትጀምራለች። ገላ ህመሟ ሳይባባስ ልጇን የምታገኝ ይመስልዎታል? ወንድማማቾቹስ በሰላም የሚኖሩ ይመስልዎታል? ግንቦት 24 ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ላይ ይመልከቱ!

ናፍቆት በሙዚቃ እና ትወና ስጦታ ያላቸውን እነዚህን ተዋንያንያኖች ያቀርብልዎታል፡

ገላ

ለሙዚቃ ያላት ፍቅር፣ ታዋቂነት እና ገንዘብ ምንም እንዳይመስላት አድርጓልታ። የሰውን ችግር ተረድታ በሙዚቃዋ ትገልጸዋለች። በድንገት በመታመሟ ልጇ ያአብቃልን ለማግኘት ጥረት ታደርጋለች።

ቃላብ

ቃላብ ቤተሰቡን ይወዳል ግን ከጉዲፈቻ መታ አብራ ላደገችው እህቱ ባለው ፍቅር ከቤተሰቡ ጋር ሲጣላ ከቤት ይጠፋል። ስለ እናቱ እና ስለሚያፈቅራት ልጅ እያስታወሰ እርቆ መኖር ይጀምራል፣ የእናቱንም መታመም አያውቅም።

ጸሀይ

ጸሀይ ለእናቷ ገላ ያላት ፍቅር በጣም ጥልቅ ነው፣ እናቷን ለማስደሰት በቤት ውስጥ ስራ ትረዳታለች የሙዚቃ ስራም አብራት ትሰራለች። የገላ እና የጸሀይ ቅርብ ግንኙነት ከቤተሰብ እና ከሙዚቃ ያላቻው ፍቅር ይመነጫል።

ግሩም

ወንድሙ ቃላብ ለጸሀይ ያለው ፍቅርን አይወደውም እና እናቱ ያአብቃልን ማፈላለጓን አይፈልግም። ግሩም ጸሀይን ከሱ ጋር ብቻ እንጂ ከቃላብ ጋር ማየት አይፈልግም።

 

እነዚህ ልብ አንጠልጣይ ድራማዎች በአቦል ቲቪ አያምልጦ! ዙረትን ሰኞ ከምሽቱ 02:30 እና ናፍቆትን ማክሰኞ ከምሽቱ 02:30 ይጠብቁ!