Logo
Gojwachin S1 Slim Billboard Desktop
channel logo

Gojwachin

466Reality13

የእነዚህ የአቦል ቲቪ ገጸባህሪያትን ታሪክ መቀየር ቢችሉ እንዴት ይቀይሩታል?

ዜና
24 ማርች 2022
ምርጫዎን ያሳውቁን!


የአቦል ቲቪ ገጸባህሪያት አሁን ላሉበት ቦታ ያደረሳቸው የተለያየ ምርጫ ነበር። ከእነዚህ የተለያዪ ምርጫዎች ውስጥ ታሪካቸውን ቀይረዋል ብለን የምናስባቸውን ጊዜያቶች ዘርዝረናል። እርሶም ምርጫ በመምረጥ  የእነዚህ ገጸባህሪያትን ህይወት እንዴት እንደሚቀይሩ ያሳውቁን!

ሁንአንተ አደይ እንድታገባው ለመጀመሪያ ጊዜ ጠይቋታል። አቶ ታደሰ ሁንአንተ ለእሷ ጥሩ ባል ነው ብለው ያስባሉ ግን አደይ ለአቤል ያላትን ፍቅር መርሳት አልቻለችም።

በናፍቆት ድራማ ላይ ፀሀይ እና ግሩም በመሃላቸው የነበረውን የፍቅር ግንኙነት ሲደብቁ ቆይተዋል። ግሩም ለገላ እውነቱን መንገር ይፈልጋል ግን ፀሀይ ለእናታቸው ሲሉ ቢጠብቁ (ዝም ቢሉ) ይሻላል ብላ ታስባለች።

በመዘዝ ድራማ ላይ መሳይ ጌታሁንን በመርዳቱ የእራሱ እና የተለያዩ ሰዎች ህይወት ተመሰቃቅሏል። እናም መሳይ ንጽህናውን ለማስመስከር ባደረገው ጥረት ወንድሙ እና እጮኛው ተጎድተዋል።

በየተገፉት ድራማ ላይ የሊንዳ ህይወት አቅጣጫውን የቀየረው እናቷ እስርቤት ውስጥ የተገደለች ቀን ነበር። በዚህ ምክንያት ሰራተኛ መስላ የጴጥሮስ ቤት ለስለላ ገብታ ነበር። ይሄ ምርጫዋ የማኪን እና ቶማስን ህይወት አደጋ ውስጥ ከቶ ነበር።

እነዚህ ምርጫዎች ቢቀየሩ ምን የሚሆን ይመስለዎታል? ሀሳብዎን በኮመንት ያሳውቁን!

ለበለጡ ልዩ ታሪኮች አቦል ቲቪን በዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!