Logo
Eshururu S1
channel logo

Eshururu

465ComedyPG13

የአቦል ቲቪ አዲስ አስቂኝ አቅርቦቶች እሹሩሩ እና የጨረቃ ሳቆች

ዜና
16 ጃንዩወሪ 2024
ጥርን ከአዲስ አስቂኝ መዝናኛ ጋር ይቀበሉት።
eshururu and yechereka sak article

እሹሩሩ

"እሹሩሩ" ኮሜዲ ድራማ ተወዳጅ ተዋንያን ሽዋፈራው ደሳለኝ (አቶ አኩዬ)፣ ሚልዮን ብርሃኔ (መላኩ)፣ ንፁህ ሀይሌ (ይርገዱ) እና ሄኖክ አለማዬ (ዝናቤ) ይዞ ቀርቧል። ድራማው ስለ አቶ አኩዬ የተባሉ የወረዳ አስተዳዳሪ እና የድሮ ጓደኛቸው ፊትአውራሪ በሰጧቸው አስቸጋሪ ስራ ነው። አቶ አኩዬ ሴት የሚፈራውን የፊት አውራሪን ልጅ መላኩ እንዲያገባ ማድረግ አለባቸው። ይሄን ካላሳኩ ከወረዳ ስተዳዳሪ ስራቸውን ፊትአውራሪ እንደሚያባርሯቸው ሲረዱ አቶ አኩዬ መላኩን ለመዳር የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ ይጥራሉ።

በዚህ መሀል አረቄ ካልጠጣ ምንም ማስታወስ የማይችለው የአቶ አኩዬ ጠባቂ እና ወሬ የምትወደው ልጃቸው ይርገዱ፣ አቶ አኩዬ መላኩን ለመዳር ለሚያደርጉትን ጥረጥ እንቅፋት ይሆናሉ። አቶ አኩዬ መላኩን መዳር ይችሉ ይሆን?

የአቶ አኩዬን ታሪክ በእሹሩሩ ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉት!

የጨረቃ ሳቆች

“የጨረቃ ሳቆች” የምጸት ኮሜዲ ድራማ ሲሆን ታሪኩ በዋናነት የሚያተኩረው አዲስ አበባ ቦሌ አካባቢ በሚገኝ አንድ ባለቤትነቱ የግል ባለሀብት የሆነ የማታ ትምህርት ቤት ላይ ነው። ናሳ አካዳሚ ጥሩ ኑሮ ያላቸው ከሚማሩበት ትምህርት ቤቶች አንዱ ሲሆን በማታው ክፍለ ጊዜ ሀብታም ቤት ተቀጥረው የሚሰሩ እና ጥሩ ደረጃ ላይ የሆኑ ከዚህ ቀደም መማር ባለመቻላቸው ምክንያት አሁንም ቢሆን ትምህርትን እንበቀለዋለን ያሉ ተማሪዎች የሚማሩበት ትምህርት ቤት ነው።

በናሳ ትምህርት ቤት የሚቀርቡት ልዩ ልዩ ተማሪዎች የተለያየ አኗኗር፣ እድሜ እና አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው። ተማሪዎቹ ያላቸው የተለያየ ባህሪ ሲቀላቀል አስቂኝ እና አስተማሪ ሁኔታዎችን ይፈጠራል። ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ እንግዶች እውቀታቸውን ለማካፈል ወደ ትምህርት ቤቱ ሲመጡ ያልተጠበቁ ክስተቶችን እየፈጠረ የሚያዝናና አቅርቦት ነው። የጨረቃ ሳቆችን ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 1፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!