Logo
Afaf S1

የመከራ ሌሊት አያልቅም – አፋፍ

ዜና
23 ጃንዩወሪ 2024
እስከዳር የቀበረቻቸው ምስጢሮች ተቀብረው አይቀሩም። በዚህ ሳምንት በአፋፍ እስከዳር አንዱን ስትል አንዱ እየፈተናት ነው።
afaf article - when it rains it pours

እስከዳር መታፈሪያ ስሟን በክብር እና ምርጥ ስራ ስታስጠራ ኖራለች ነገር ግን ይህ በጥንቃቄ የተመሰረተው ህይወት ከጀርባው ብዙ ምስጢር ደብቋል። ባለፈው ሳምንት ክፍሎች እስከዳር በድሮው ህወቷ ተሰናብታው የነበረውን ፣ የአሁን ማንነቷ ላይ ትልቅ ተፅኖ ያለው ከድሮ ፍቅረኛዋ አብዮት ጋር ተገናኝታለች።

አብዮት፣ እስከዳር ልጁን ይዛ ከጠፋች በኋላ ስለኖረው ህይወት ምንም ባይታወቅም፣ ወደ ሽቱ ቤት የገባው ስካር እና ቁጭት ይዞ ነው። ይህ ባህሪው ያልገባቸው የሽቱ ልጆች የቻሉትን በማድረግ ሊረዱት ይሞክራሉ። ከእነሱም መሀል የቀረበችው እንቆጳ፣ እስከዳር ትታት የጠፋቻት የአብዮት ልጅ ነች። እናም ይህን ሚስጥር የማያውቁት አባት እና ልጅ እየተቀራረቡ ይሄዳሉ። በዚህ መሃል የቤተሰቡን ሀዘን የተረዳው አብዮት የእስከዳርን ማንነት ሳያውቅ ሊያገኛት ይወስናል። አብዮት፣ እስከዳር፣ ወንድም እና ጓደኛውን ዋሴን ለኦፓል ብላ እንደገደለች ይረዳል እናም ከንዴት የተነሳ ሊገላት ይሞክራል።

እስከዳር ከአብዮት ማምለጥ ብትችልም የድሮ ፍቅረኛዋ መመለስ እና የሰራችው ክህደት መታወቁ ትልቅ ድንጋጤ ውስጥ ከቶ እንድታመም ያደርጋታል። ይሄን ጭንቀት ለመቋቋም ስትሞክር በመከራ ጨረታውን ያቋረጠችበት አሌክስ ኦፓል ለበቀል ይነሳል። በተጨማሪም አብዮትን እውነቱን የነገረው ታምራት ነው ብላ በማመኗ ተጎድታለች።

ይህ ብቻ ግን አይደለም! የእስከዳር የመከራ ሌሊት ላይ ሌላ መከራ የሚጨምር ክስተት ተፈጥሯል። ዳግም ሲያማክራት የነበረውን የስነ-ልቦና ባለሞያ ስለ እስከዳር ወንጀል እውነቱን ነግሯታል።

እስከዳር ይሄን መከራ ማለፍ ትችል ይሆን? ወይስ እውነቱ ተጋልጦ ለፍርድ ትቆማለች? ይሄን ልብ አንጠልጣይ ድራማ በአፋፍ ድራማ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉ!

#MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ፡ https://tinyurl.com/yc8p3xvd