በ1983 ሶስት ወታደሮች እና አንድ ጌታሁን የተባለ ደላላ ሮኬት ለማምረት የሚያገለግል ጥሬ እቃ ይሸጣሉ። ከ30 ዓመታት በኋላ ጌታሁን በሕዝብ ዘንድ ሊታዩ ስለሆነ ወታደሮቹን ለማግኘት ይወስናል እናም ጠበቃ መሳይን ይቀጥራል። መሳይ እነ ጌታሁንን ካገኛቸው በኋላ ህይወቱ ይመሰቅቃቀላል። ፖሊስ፣ ጌታሁን እና የወታደሮቹ ቤተሰቦች ጠላቶቹ ይሆናሉ። ስለዚህ ንፁህነቱን ለማረጋገጥ እና ነፃነቱን ለማግኘት መሳይ እውነቱን መፈለግ ይኖርበታል።