ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሲቃረብ፣ በየሳምንቱ በቴሌቪዥን መስኮታችን የምንመለከታቸውን፣ በፈተናዎች የማይበገሩ እና ለዓላማቸው የሚቆሙ ድንቅ ሴቶችን ልናከብር ይገባል። ከመከራ ጽናት እስከ ስኬት ድረስ፣ በአቦል ቲቪ ላይ የምናደንቃቸው አራቱ ሴቶች እነሆ፦
1. ሉሊት (ቃታ)፦ የእናትነት መስዋዕትነት እና የጽናት ተምሳሌት
ሉሊት ለልጆቿ ስትል ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ የሆነች ብርቱ እናት ናት። ልጇ በድንገት ጓደኛውን በመግደሉ ምክንያት የገጠማትን አስደንጋጭ ክስተት ምስጢር አድርጋ ለመጠበቅ የምታደርገው ጥረት ቀላል አይደለም። ጨካኝ እና በደለኛ ባለቤቷ ተኮላ ህይወቷን መራራ ቢያደርገውም፣ ሉሊት ግን ለልጆቿ ጥበቃ ስትል በጽናት መቆሟን ቀጥላለች። የእሷ ጥንካሬ በጨለማ ውስጥ ያለ ተስፋ ነው።
2. ሐረግ (ግዛት)፦ የማይበገረው የሥልጣን እና የጥንካሬ ማማ
ሐረግ የባለቤቷን ሞት ተከትሎ፣ የተገነባውን የወንጀል ግዛት እና የቤተሰቧን ህልውና ለመጠበቅ ብቻዋን የቆመች ሴት ናት። የባለቤቷ ጠላቶች እና የቅርብ ሰዎች ሊያሳንሷት ቢሞክሩም፣ እርሷ ግን በአዲስ ማንነት ተነስታ ጠላቶቿን አንድ በአንድ በማርገፍ ስልጣኗን አስከብራለች። ምንም እንኳን ተግባሮቿ ሁሌም በህግ እና በቀናነት የታገዙ ባይሆኑም፣ ለልጆቿ ያላት ጥልቅ ፍቅር እና ያሳየችው የአመራር ብቃት ግን እጅግ የሚደንቅ ነው።
3. ዕፀ-ሕይወት (ዕፀ-ሕይወት)፦ የአባቷን ፈለግ የተከተለችው ባለራዕይ
ዕፀ-ሕይወት የአባቷን የሳይንስ ምርምር እና ውርስ ለማስቀጠል የምታደርገው ጉዞ በትዕግስት እና በጥንካሬ የተሞላ ነው። በከተማ ውስጥ ካገኘችው የእንጀራ እናቷ ከሰብለ እና ከአሸናፊ የሚደርስባትን ተንኮል፣ ሴራ እና ወከባ በብልህነት ተቋቁማለች። በትግሏ በኩባንያው ውስጥ ያላትን ድርሻ በማስከበር፣ የአባቷን ስም እና ስራ በኩራት እያጸናች ያለች ብርቱ ወጣት ናት።
4. ኪም (Out and About)፦ የማትታከተው የጉዞዋ ንግስት
የጉዞ ፕሮግራማችን አድማቂ የሆነችው ኪም፣ ለጉዞ ያላት ፍላጎት እና የማይታክተው የማወቅ ጉጉት ለሁላችንም መዝናናት ምክኛት ነው። በመላው ኢትዮጵያ በምታደርጋቸው አስደሳች ጉዞዎች፣ ለምግብ እና ለታሪክ ያላት ፍቅር እና ተጫዋች ማንነቷ እያንዳንዱን ጉዞ የማይረሳ ያደርገዋል። ኪም የኢትዮጵያን ውበት ለዓለም የምታሳይ የጥንካሬ እና የደስታ ተምሳሌት ናት።
የአቦል ቲቪ ምርጥ ምርጥ ድራማዎች ከሰኞ እስከ አርብ ይቀርባሉ!
በ #MyDStv መተግበሪያ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6
በ DStv Stream መተግበሪያ የሚወዱትን ድራማዎች ይከታተሉ!
