abol tv logo

የፈዋሹ ቅጠል ፍልሚያ!

ዜና23 ፌብሩወሪ 2026
የምናብ ከተማ መነሻ ጥንት ኢትዮጵያ መዳረሻው ደጋአምባ ድራማ !
Degamba

የምናብ ምጥቀቱ የድርሰት ልኩ የትወና ጥጉ የታሪክ ፍሰቱ የኪን ይዘቱ የምስል ቅንብሩ ልዩ ያደርገዋል ደጋአምባ ድራማን በትንሽ የምናብ መንደር ላይ የታሪኩ መነሻ ሆኖ መላ ሀገሪቱን በተያያዥ ታሪኩ አካል በማድረግ እስከ አድማስ የሚዘልቀው ደጋአምባ የጥበብ ስልጣኔ ጥግ የባህል መከበር ለማህበረሰቡ ቋሚ ቅርሰንት ላይ ዋጋው ምንድረሰ እንደሆነ እና የዛሬው የአለም መርህ የስልጣኔ መነሻ ትእዛዝን ማክበር መገዛት አባቶቻን መስማት መሆኑን አስምሮ ያስረዳል

ይህ ድራማ የቀደመውን የኢትዮጵያን ታላቅነት ሚስጥር በግልጽ የሚተርክ በትንሽ መንደር አምሳያ ጥንታዊት ኢትዮጵያ የምትመሰልበት የሀገሪቱ የቀደሙ ጥበቦች በምን መልኩ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገሩ ነትበው እንደ ቀሩ የሚያስረዳ የመድኃኒት ጥበብ ከእፅዋት ጀምሮ ከስር ቅጠል ህብረት አንስቶ ወደ ትልቅ የሚዳሰሰው መድሃኒት መሸጋገሩን የሚያነሳ የጥበብ መንገድ በጋል ሲኒማቲክ ሂደቶችን በመከተል የሚቀርብ ልዩ የታሪክ ባለቤት ነው ደጋአምባ ድራማ

የዘርማያ ስር ባለቤት የፈዋሽ ቅጠሎች መገኛ ደጋአምባ ውቢት የምናብ ከተማ የተፈጥሮን ሃያልነት በተረዱ ድንቅ የሀገር ሽማግሌዎች የምትመራ ውበት የተጫጫናት ጥበብ የከበባት የሀገር መነሻ ታሪከ ብዙ ምድረ ስልጣኔ ሆና የምትዘልቅ ውብ ከተማ ናት በምናብ ያለች በህይወት የምትዘልቅ የአዋቂዎች መንደር ልሳነ ስልጣኔ የጀግኖች መገኛ ልዩ ስፍራ በደጋአምባ ድራማ ውስጥ የኮኮብ መውጣት የወቅት መለዋወጥን ተከትሎ የሚከሰት የክፉ ቀን ምሳሌ መጥፎ የታሪክ ግጥሚያ አለ ዘርማያሰባህ ይህ ክስተት የሃያ ስምንት አመት ውጤት የክፉ ቀን ምሳሌ ነው በሌሎች የመንደሩ አባላት ደሞ የድህነት ምልክት የተስፋ ዘመን አምሳያ ተደርጎ የሚቆጠር ሙላት የፈሰሰበት ልዩ ቀን ነው ድራማው ስለዚህ ጉዳይ በግልፅ ይተርካል በሁነት ያስረዳል በልዩ መልኩ

በዚህ ድራማ ውስጥ የትውልድ እና የጥበብ መሸጋገር በልዩ መልኩ ይታያሉ ሁሉም የዘውግ ወይም የመንደር መሪዎች በልዩ መልኩ ጥብብ ለማሻገር ለቀጣይ መሪ ምርጫ ላይ ሲቸገሩ የሚያሳይ ባለ መሉ ታሪክ ፊልም ነው

የጥንቱን የኢትዮጵያን የስልጣኔ ገናናነት የዛሬ ትውልድ የተከተቡ የታሪክ ድርሳናትን አገላብጦ በማንበብ ይህ ነው የኛ ታሪክ ማለት ላይ ብዙ እንደ ሚቀረው በአያሌ የማህበረሰብ ባለሞያዎች የሚነሳ አብይ ማህበራዊ ስብራት ነው

በዘመነ ግሎባላይዜሽን አለም ወደ አንድ መንደር ጉዞ ላይ ከምዕራቡ እስከ ምስራቁ እስያ ከእርሱ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ድረስ የነበረውን የዘመን ገድለ በትውልድ ወርቃማ ቅብብሎሽ የተገኘውን ድል ወስልጣኔ በፊልም መልኩ ዛሬ ላለው ትውልድ ሲሰንዱ ለተቀረው አለም እኛ ማለት እንዲ ሲሉ በኪናዊ መንገድ እራሳቸውን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ

በዚህም አለም ስለ ራሳቸው ከራሳቸው አንደበት መስማት ይዟል ደጋአምባ ድራማ የኢትዮጵያን የጥንት ማንነት በሚገባ የገለፀ የስልጣኔ ምጥቀትና ሙሉነትን በምናብ የተፈጠረች ከተማ ላይ መስሎ ለዛሬ የዘመን ባለቤት የጥንቱ በማዋዛት የመረዳት ብዥታን የማጥራት ሂደት ላይ ባለ ድርሻ ሆኖ የሚታይ በጉጉት የተሞላ በድንቅ የትወና ብቃት የታጀበ ልብን ሰቅዞ የያዘ ምትሃታዊ ድራማ ቢባል አያንስበትም ደጋአምባ ድራማ

ደጋአምባ ድራማ የምናብ ከተማ ውስጥ ልዩ የታሪክ ማእዘናት በመፍጠር የጥንት ኢትዮጵያን ስልጣኔ በወጉ የሚተርክ ድንቅ ድራማ ነው በልብ አንጠልጣይ ታሪክ ታጅቦ በሁነት ሳይሆን በምክንያትነት የሚመራ የጥበብ መንገድ ጠቋሚ ልዩ የታሪክ የመቼት ድምቀት የሚረታው ልዩ ድራማ ነው