ደጋአምባ ተከታታይ ልብ አንጠልጣይ ድራማ ላይ ገንዘብ የፍላጎት መነሻ ነው ፣ እቅም የደስታ መነሻ ፣ ፍቅር የፈተና ሜዳ ፣ ሃቅ የትግል ውጤት ፣ እገታ የስልጣን ማሳያ ፣ ሃዘን የአቅም ማጣት ምልክት ትልቁ ጥበብ ማገልገሉ ቀርቶ የግል ጉዳይ ሆኗል በዚህ ተከታታይ ሚስጥር የሞላው ድራማ ላይ ህይወት ይፈተናል በቅርብ ሰው በኔ በሚሉት አማካሪ ጭምር ይሄን ውስብስብ ጉዳይ በሚገርም የሲኒማ ጥበብ ሸምኖ በማይሰለች አቀራረብ በተወዳጁ አቦል ቲቪ አስተማሪ ሆኖ እንደቀጠለ ነው ።
የኢትዮጵያውያን የጥንት ጥበብ ሳር መማስ ፣ ቅጠል መበጠስ ድሮ ድሮ ከማህበረሰቡ የሚያስገልል በክፉ የሚያስነሳ ድንቅ ጥበብ ነው ይህን ሂደት በሚገርም ጥበቡ ጠቃሚ መሆኑን በሚያሳይ መልኩ የሚተርክ ድንቅ ድራማ ደጋአምባ በስው ልጅ ህይወት ላይ ስልጣን እና ገንዘብ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው እና ፍላጎትን መግታት ካልተቻለ ዋጋው ትልቅ መሆኑን የሚያሳይ ድንቅ ድራማ ነው ።
በዚህ ድራማ ላይ የአባቷን የመድሃኒት ጥበብ ለሀገር ይዋል ለዜጎች ይበርከት የምትለው ፍካት የስሟ ትርጉም በግብር የሆነላት ይቅርብ ነው ባለችው ሰው የፍላጎት ገደብ ማጣት አማካኝነት ትልቅ ፈተና ገጥሟታል ይህን ለማስተካከል የምታደርገው ትግል ላይ በሷ በኩል የሆነው የልብ ሰው ፍቅረኛ ሰውመሆን
ይህ ሂደት ይሳካ ይሆን ድራማው መልሰ አለው ።
በዚህ ልብ አንጠልጣይ ድራማ ውስብስብ ታሪክ በግል የሚታይበት ገንዘብ ፣ ከስልጣን ጋራ በፍልሚያ የሚዋደቅበት የሰው ልጅ ክፋት እና ደግነት በግልጽ የሚታይበት የአለም አሰራር በልኩ መቃኘት ካልቻለ ጥፋቱ የጋራ መሆኑ በግል የሚታይበት ነው ደጋአምባ ድራማ ።
በዚህ ድራማ ውስጥ ሁሉ ሰው በየ አመሉ የራሱን ህይወት መምራት በከበደው ግዜ አለም መፈንጫ ህግ መግደያ ነው ፣ እና ይመርን የመሰለ ለባህል ለሀገር የሚተጋ ድንቅ ሰው በመኖሩ አለም በተስፋ የተሞላች የደግነት ልክ ለሁለንተናዊ ለውጥ ዋጋ እንዳለው ያሳየበት ደጋአምባ ድራማ የዚህ አለም ከንቱነት በርህራሄ የሚተካ ነው የሚለው በጥልቅ የሚያሳይ ነው ።
ደጋአምባ ላይ ይመር ወግ አጥባቂ ነው ፣ ሰውመሆን የፍቅር ሰው ፣ ፍካት የአባቷን አደራ ታሪክ ለማስቀጠል የምትተጋ ልብ እንስፍስፍ ፣ ምስራቅ የስጋ ፍላጎቷ ከነብሷ ያጣላት ወግ አልባ ናት ይህም የሁሉም ኢትዮጵያውያን የቤት ባህሪ ግልባጭ የህይወት መልክ ማሳያ ትልቅ መማሪያ ያደርገዋል ደጋአምባ ድራማን ።
ይህ ድራማ የጥበብ ልክ ፣ የሰው ልጅ ማሳያ ፣ የባህሪ ግብር መለያ የፍቅር እና የገንዘብ መታያ የህይወት ግብር ምላሽ መደምደሚያ ትልቅ የታሪክ አስተማሪ ነው ደጋአምባ ድራማ ።
