የዕፀህይወት ድራማ ትኩረት ሳቢ የገፀ ባህሪ ሁሉ የፊት የሚባለው በተንኮል ደረጃም የላቀው በሁለት መለያ የሚጫወተው አሸናፊ በዚህ ድራማ ውስጥ እልም ያለ ቀጣፊ ማስመሰል የተዋጣለት ሁሉም ቦታ ላይ አለው በሚል ወዳጅ መስሎ ጠላት የባህሪ እስስት ሆኖ አሁን ላይ የዕፀህይወት ፍቅረኛ የልብ ሰው ሆኖ በሰብለ የተንኮል ሴራ ተክኖ ቤተኛ ሆኗል ነገር ግን የሴራ ጥግ የማይጥላት ዕፀህይወት የአሸናፊን እና የሰብለን ተንኮል ተረድታለች ።
አሸናፊ በማስመሰል የተዋጣለት ነው ሁሉንም ሃሳብ በማስመሰል ነው የሚያልፈው ከፅህይወት ጋር ያለው ግንኙነት ጭምር በእስስት ባህሪው ወዳጅ መስሎ መቅረቡ ዕፀህይወትን ዋጋ በማስከፈል እረገድ ሚናው ትልቅ ነው ይህ ገፀባህርይ ለጥቅሙ ሲል የማያደርገው የለም ፍላጎት ከነብስ የሚበልጥበት የባህሪ ልዩነት ግድ የማይለው አስመሳይ ባህሪ ያለው ነው በመሆኑም የሰብለን ልክ ያጣ ፍላጎት ለመሙላት በማሰብ ፍቅረኛ እያለሁ መቅረቡ የእሱን እና የሰብለን የሃብት ፍላጎት መጠን የሚያሳይ ነው ።
እነ ሰብለ ከተንኮል ጋር በማበር ጭምር የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ አይናቸውን በማጉረጥረጥ ፍላጎት ለማሟላት ሲሉ ብቻ ከሁሉም ሰው ጋር ሃሳብ ሳይኖረው ነገሮችን በእሽታ ብቻ በመቀበል ታሪክ አልባ የሰው አገልጋይ ፍላጎት ፈፃሚ ሆነው ዕፀህይወትን ለማምከን በሚል ጋራ ሸንተረረ እየወጡ ይገኛሉ ፣ የህይወት ምህዋር በራሷ ላይ ያረፈው ዕፀህይወት ነገሮችን በጥበብ በማለፍ የራሷን ታሪክ በዚህ ድራማ ላይ በደማቁ እየፃፈች ትገኛለች ።
አሁን ላይ ዕፀህይወት ድራማ በአስገራሚ ክስተት ታጅቧል የሰብለ የዘላለም እቅድ የተሳካላት ይመስላል የሃብት ነገር የስም እና የዝና ውጤት የክብር ፍለጋው ጉዞ ለነ ሰብለ የሰመረ ይመስላል ፣ የአባት አደራ የቤተሰብ ታሪክ አስቀጣይ ዕፀህይወት ደሞ ነገር ህይወት መስመር የሳተባት የምትሳሳለት ሁሉ ለመውደም የተዘጋጀበት ከባድ የታሪክ እጥፋት አልፋ የመድሃኒት ቅመማ ስራ አደጋ ውስጥ መሆኑ ተነግሯት ወደ ቀደመው ስራ ለመመለስ እያግባቧት ይገኛሉ ለዚ ጥያቄ ምላሽ ትሰጥ ይሆን ድራማው መልስ አለው ።
እውነት ወይስ የሴራ ውጤት ያሸንፋል የሚለው ጭምር በዕፀህይወት ድራማ ውስጥ ተገማች መሆን አልቻለም በቀጣይ ምን ይፈጠር ይሆን ? ድራማው መልስ አለው ።
ከዚህ ቀደም ሰብለ እና ግብረ አበሯቿሁ ዕፀህይወትን ለማጥፋት መሳሪያ ደግነው እሷን ለማጥፋት ሙከራ አድርገው ሊሳካ አልቻለም እንዲሁም የዕፀህይወት የስራ ሰነድን በሙሉ አቃጥለው ያለ ማስረጃ የስራ ንድፍ አስቀርተዋል ይህ ለዕፀህይወት እጅጉን ከባድ የህይወት ስብራት የኋላ ጉዞ ጅምር ነበር ነገር ግን ዛሬ ይሄን ማለፍ ችላለች አሸናፊ የሰብለ ልጅ ፍቅረኛ ሆኖ ዕፀህይወትን ለመጣል አሲሯል ይህ የተንኮል ጥግ ነው የሴራ ካባ ጭምር ይሳካል ግዜ መልስ አለው ።
ሰብለ ከራሷ ጋር ማውራት ሲጀምር ወደ ራሱ መመለስ ሲጀምር ምን መልሰ ይኖረው ይሆን ።
አሸናፊ እና ሰብለ ተፈጥሮን መሆን አልቻሉም ራስን መሆን ማለት፣ ማንነትን ተቀብሎ፣ ሳይደባብቁና ሌላውን ሰው ለመሆን ሳይሞክሩ በነጻነት መኖር ማለት ነው ግን አሸናፊ እና ሰብለ መሆን ተሳናቸው ።
ራስን የመሆን ጉልበት የሚመነጨው ማንነትን በመቀበል ነው በራስ መርካት ጭምር የሚመጣው በዚህ ልክ ነው ።
አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ስለማይቀበሉ ራሳቸውን ሆነው መኖር አይችሉም ራሱን መቀበል ያስቸገረው ሰው ላይ የሚታየው የመጀመሪያው ምልክት ራስን አለመሆን ነው፤ የማይቀበሉትን ማንነታቸውን ለውጠው ለመታየት ሲሞክሩ ራሳቸውን ያገኙታል አሸናፊ እና ሰብለ በዚህ ልክ የተዋቀረ ማንነት ባለቤት ናቸው ።
ዕፀህይወት ድራማ በታሪክ ፍሰት ታጅቦ ፣ በሴራ ተከቦ የህይወት ቅያስ ይዞ ቀጥሏል በቀጣይ ምን ይፈጠራል ግዜ መልስ አለው ።
