ፍላጎት ከነብስ የበለጠበት ዕፀህይወት ድራማ የልጆች ትግል የቤተሰብ ታሪክ ለማስቀጠል የሚደረግ ትንቅንቅ ልጆችስ ለዚህ ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ በምን መልኩ ይተጉ ይሆን ሆይ የሚለውን ውስብስብ የተጋድሎ ምዕራፍን የሚተርክ ወዳጅ ፣ ዘመድ ቤተሰብ በህይወት ውስጥ ምን ያህል ወሳኝ መሆናቸውን በግልፅ የሚያሳይ በሚገርም የምስል ቅንብር የተዋበ ድራማ ነው ዕፀህይወት ድራማ። በዚህ አስገራሚ ድራማ ነገሮች በፍጥነት እየተቀየሩ ነው ዕፀህይወት የአባቷ ንብረት ወራሽ ለመሆን የሚያበቃትን የኑዛዜ ደብዳቤ በቀጣይ የድራማው ትንቅንቅ ልታገኘው ትችል ይሆን ዕፀህይወት በቀጣይ መልሰ አለው ፣ ለወትሮው የምድር ህይወት ባለ ብዙ መልክ ነው የቅርብ ያሉት የሩቅ ሲሆን መመልከት ፣ የሩቅ ዋጋ አልቦ ሰዎች ደሞ ባልተገመተ ሰአት እና አጋጣሚ ደራሻ ባለውለታ ሲሆኑ ማየት የምድር ጉራማይሌ ገፅታን በመልክ ያሳያል። ዕፀህይወት የሃብት ተካፋይ መሆን የለባትም በሚል ሌላ ተቀናቃኝ በግራ በኩል ብቅ ብላለች ሰብለ ከባሏ ፍቃዱ ሞት በኋላ የድርጅቱ ወራሽ መሆኗን ለቦርድ አባላት ብታሳውቅ እውነት አሸናፊ ነው እና ጠበቃ ሰውነት ዕፀህይወት የድርጅቱ ግማሽ ሀብት ወራሽ መሆኗን ያስረዳል። ሰብለን የሃብት ማማ ላይ የሚሰቀለው አጋጣሚ በጠበቃ ሰውነት ከሽፏል ምን ይሆን የዕፅህይወት ቀጣይ ፈተና ድርጅቱን ከመምራት እስከ ታሪክ ማስቀጠል ያለው ከባድ ጉዞ በምን ይታለፋል እንዲሁም የሰብለ እልህ የተሞላበት የተሸነፍኩ ስሜት በምን ባህሪ የበቀል እርምጃ ይጓዝ ይሆን ድራማው በቀጣይ ክፍለ መልሰ አለው ። በዚህ እውነተኛ የህይወት ሌላውን መልክ በሚተርከው ድንቅ ድራማ እንዴት ለምን ፣ የሚያስብለው እስክንድር ገፅ ባህሪ የነ ዕፀህይወትን ቤት በእሳት ያወድማል ይህም የነ ሰብለ ሌላው እቅድ መሆኑ ነው ፥ ማስገረም ልማዱ የሆነው ዕፀህይወት ድራማ ህይወት ፈተናው ብዙ ጉዞው አድክም ፣ ውል አልባ ይሆናል በዚህ ግዜ እንዴት ፈተናን ማለፍ እንደምንችል ያሳያል ዕፀህይወት ድራማ በሁሉም ክፍል ። የዕፀህይወት ፈተና ፈርጀ ብዙ ነው የሚታለፍ የማይመስል አስገራሚ እንዴት የሚያስብል ታድያ እነ ዕፀህይወት ይህን የውስጥ መከዳት የሃብት ሽሚያ እንዴት ትለፍ የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው ወገብን ሸብ በማድረግ በፅናት በመቆም የጀርባ ሴራን በመረዳት በብልጠት በሃሳብ ክህሎት ማለፍ አማራጭ የሌለው ውሳኔ ነው ። በምድር ሲኖር እልፍ አስቸጋሪ የስኬት ፣ ሁለንተና መኖር ላይ ችግሮች አሉ መፅናናት እና መፅናት ደሞ የዚህ ችግር የመፍትሔ መንገድ ናቸው እነ ዕፀህይወት ደሞ የባህሪ ግብር ያላቸው እውነተኛ ሰው ሲሆኑ እውነትን የያዘው ደሞ አሸናፊ ይሆናል ። ዕፀህይወት ያጋጠማት ፈተና በእውነቱ ከባድ ነው ግን ትወጣ ይሆን ግዜ ደጉ ድራማው መልስ አለው ። ፍቅር ፣ እምነት ፣ ክህደት ፣ እውነት ፣ ቤተሰብ ፣ ሃብት ፣ በአንድ የህይወት ሜዳው ላይ በግልጽ እና በጀርባ እንደ ባህሪያቸው ገጥመው ከባድ ፍልሚያ ውስጥ ናቸው በዕፀህይወት ድራማ ማን ከማን በቅድመ ተከተል ተፋልሞ ተሸነፈ ፣ አሸነፈ ለሚለው ድራማው መልስ አለው ። ዕፀህይወት ደራማ የመልክ ገፁን በወጉ ይዞ የፍላጎትና የደስታን ልክ በወጉ የሚተርክ ድንቅ ድራማ ነው ። ጓደኝነት በዝና ሲፈተን የሚያሳይ ድራማ ፓይለቶቹ ! የልጅነት አብሮ አደግን በዝና አማካኝነት ያለፈውን ድንቅ የማይረሳ የሚመስለውን የልጅነት ወርቃማ ዘመን በታሪክ የሚፃፍለት ያስባለውን ግዜ በሃብት እና ዝና አሽቀንጥሮ በመጣል ሁሉንም የሚያኖር ታሪክ በመርሳት የስራ ስኬት የሚያስቀናው ሆኖ ወዳጅ ጠላት ሆኖ በሃይል የሚታገልበትን ሂደት የሚያሳይ ድራማ ነው ፓይለቶቹ ። የልጅነት አብሮ አደግ ፣ በከፍታ እና በዝቅታ የታለፈ ታሪክ ያለቸው ሁለት በተለያየ የኑሮ ደረጃ ላይ ያደጉ ልጆች በአዋቂነት እድሜ ላይ የኖሩለትን ህልም ለመኖር ሲሉ በቅናት መንፈስ የቅናት ጎራ በመለየት ህይወትን የትግል ሜዳ አድርገው በትግል ላይ ናቸው በፓይለቶቹ ድራማ ፣ በዚህ ድራማ የሃብት ማማ ላይ ያደገው ሌላው ህልሙን በመኖር ላይ የሚገኘው ፓይለት የወዳጁን ህልም ለማክሸፍ በሚመስል መልኩ ሌላ የህይወት ምዕራፍ ላይ የሚገኘውን ወዳጁ በቅናት መንፈስ በመነሳት በእውቀት ለማኩሰስ ሲል በቅናት ተነስቶ ለመጣል የሚያደርገው ጥረት በድንቅ የታሪክ ፍሰት የምስል እና ቅንብር ውጤት አጅቦ የሚያሳይ ነው ፓይለቶቹ ድራማ ። በዚህ ድራማ ላይ ያሉ ሁሉም ድራማዊ ክስተቶች የልጅነት ህይወትን የሚተነትኑ የህይወት መልክን እና የዘመን አሰራርን የሚተርኩ ድንቅ የመቼት መልክ ሆነው ሁለቱን ወዳጆች የሚያስታርቅ ታሪክ ሳይሆን የሚያራርቅ ተግባር በአንድ ጎን እየተሰራ ወዳጅ መስሎ ጠላት ምን ማለት እንደሆ የሚያሳይ ድራማ ሆኖ የሚቀጥል ነው ፓይለቶቹ ። በሰው ልጅ ህይወት ላይ የሰው ዋጋው ትልቅ ነው ለስኬት ፣ ለትምህርት ፣ ለሁሉም ነገር ውጣ ውረድ ሰው ፍፁም አስፈላጊ ነው ሆኖ ግን የሰው ልጅ የሚጎዳው በራሱ ሰው አማካኝነት ነው ይህም የቅርብ ሰው ለስኬት አጋዥ እና ለውድቀት መነሻ ነው ይህም ድራማ ፓይለቶቹ ይህን የሰው ልጅ ህይወት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ እና ለሃላፊነት መትጋት ምን ማለት እንደሆነ ጭምር ይተርካል ። ፓይለቶቹ ድራማ የሰው ልጅ በተስፋ ከተሞላ ብቻ ሳይሆን በአላማ ከፀና ማሸነፍ እንደሚችል የሚያሳይ ጭምር ነው በውስጥ ፍቅር መቃጠል የአደባባይ በቀል እንደሚሆን የሚያሳይ ጭምር ፓይለቶቹ እነሆ በዚህ አስደናቂ ድራማ ውስጥ የሚታዩ ክስተቶች የሰው ልጅ የፍላጎቱ ተገዢ ከሆነ የመፅናት ሃይሉ ትልቅ መሆኑን ጭምር የሚተርክ ነው እንዲሁም የሰው ልጅ የሰላም መንገድም ቢሆን ዋጋው ትልቅ ስለመሆኑ በወጉ ያነሳል ድራማ እና ክስተቱን መከታተል የህይወት መማሪያ ጭምር ህያው ምሳሌ ነው ፓይለቶቹ ድራማ ። የገንዘብ ፍቅር ሁሉንም ያስረሳል በግዛት ድራማ ! በግዛት ተከታታይ ድራማ የገንዘብ ፍቅር እና የሰው ልጅ መስመር ካላ በጁ ሂደቱ እጅግ አስቸጋሪ ፣ ከባድ መሆኑን የሚያሳይ ድራማ ነው ግዛት እንዲሁም የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ምንጭ ነው የሚለውን የህይወት መርህ የረሳ ክስተት በአንዲት የታሪክ ዘዋሪ ሃረግ በተባለች ልዩ ፍጥረት የገንዘብ አምላኪ ሴት የጡዘት ልኩን የምታከር ልዩ ፍጥረት አማካይነት ግዛት ድራማ በታሪክ ከሮ ሌሎችን አጃቢ በማድረግ በምስል ቅንብር ውበት ተሞሽሮ በልኩ የቀረበ ድንቅ አስገራሚ የሚባል ታሪክ የማይገዛው ድራማ ነው ግዛት። ሃረግ የተባለች የገንዘብ አፍቃሪ ስለ ነዋይ ብላ የገዛ የትዳር አጋሯን የገደለች ፣ የልጇን ፍቅር ጭምር ለግል ጥቅም የምታውል ልዩ ፍጥረት ነው የታሪክ አቀጣጣይ የድራማው ንግስት ይቺ ሴት በዚህ ድራማ ላይ የማይታይ የምትዳስሰ የገዛ ቤተሰቧን ስለ ገንዘብ በማለት የመግደል ጀግንነት የተላበሰች የፍቅር ፣ ዋጋው የማይገባት ከገንዘብ ይልቅ እውቀትን እና ጥበብን ለማሳደድ ብዙ ጥረት የማድረግ ጀግንነት የሌላት ፍቅረ ነዋይ የገዛት ክፉ ሴት። ጠቢቡ ሰሎሞን ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ። ከፍ ከፍ አድርጋት፤ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ ብታቅፋትም ታከብርሃለች። ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፤ የተዋበ ዘውድንም ታበረክትሃለች ሲል ተናግሯል ገንዘብ ግን የእኩይ ተግባር መነሻ ናት በማለት ከሰለሞን ውጪ ብዙ መፅሐፍት ያነሳሉ ይህን መመሪያ የማታውቀው ሃረግ ገንዘብ አስክሮ ሲደፋት የሚያሳይ ድራማ ነው በግዛት ሁሉ አይነት የባህሪ ስብጥር አለ መተኛት መነሳት ምክንያት የሆነለት እና በዘርፍ ውስጥ ያለውን ሂደት ደሞ መከተል ያቃተው በሌላ እረድፍ ላይ ደሞ በክፋት ይታያል ። የአንድ ጎልማሳ ጤነኛ ሰው አዕምሮ በአማካኝ 2.5 ሚሊዮን ጌጋ ባይት ፋይል መያዝ የሚያስችል አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ። የሰው ልጅ ይህን አዕምሮውን ስርዓት ባለው ትምህርት በመታገዝ ተሸቀዳድሞ በመልካም እውቀትና ጥበብ ካልሞላ እንደ ተንኮል፣ ቅናት፣ ጥላቻ፣ ግድየለሽነት፣ ዘረኝነት፣ ምቀኝነት፣ ስግብግብነት፣ አድርባይነት በመሳሰሉ የሕይወት እንከኖች የመሞላት እድሉ ከፍተኛ ይሆናል ሃረግ እራሷን ለገንዘብ በማስገዛት የመኖር ዋጋው እውነት ዝቅ እንዲል አድርጋለች ይህም ባህሪ ሆኖ የሰው ልጅ ላይ የሚጨክን አንጀት ይዛ በክፉ መንፈስ በመጓዝ ላይ ናት የግዛት ድራማ ይህን ህይወት በኪን ጥበብ ከፍ አድርጓ የሚያቀርብ ነው ። በግዛት ድራማ ላይ ያሉ ድንቅ የታሪክ ምስሎች የገሃዱን አለም የሚያሳዩ ናቸው በዚህ ድራማ ውስጥ የሰው ልጅ በህይወቱ የመኖሩ ነገር ለአላማ ሲሆን እና በገንዘብ ሲሸነፍ ምን ይመጣል የሚለውን ለማየት ከፈለግን ይህን ድራማ ማየት በቂ ነው ገንዘብ ኖሮክ አሰተዳደሩን ወይም አጠቃቀሙን ካላወቅክ የገንዘብ ሀያልነት አንተ ላይ ሲሰራ ይታያል እንድትገዛበት እንድትገበያይበት የተፈጠረው ነገር አንተን ሲገዛ ይገኛል ያኔ ገንዘብክ የአምሮክን ባዶነት ልትሸፍነው በማትችለው መልኩ ይታያል ይህ ደግሞ አጠቃቀምን አለማወቅ ነው ክፋቱ ያንተ ታውሮ የሌሎችንም ማሳወሩ ነው በሚል ይነሳል ሃረግም የዚህ ሃሳብ ባለቤት ናት በቀጣይ ሃረግ በገንዘብ ጉዳይ ማንን ታስገድል ይሆን ድራማው መልስ አለው ። ገንዘብ ኖሮክ ደግሞ አጠቃቀሙን ስታውቀው ግን ገንዘብ መጠቀሚያ እንጂ የአምሮ ወይም የአሰተሳሰብ ልዕልናክን አሊያም ዝቅጠትን የሚያጋልጥ ሳይሆን አንተን የሚያገለግል ስለሚሆን አንተን ጠቅሞ ሌላውን ይጠቅማል ይህን ሃሳብ በግልጽ የሚተርክ ድራማ ነው ግዛት እራሱን በሃረግ መልክ ውስጥ ከቶ ። ገንዘብ በራሡ የማንም የአእምሮ ራቆትነት ብሎም የአስተሳሰብ ልዕልናን አያሣይም ሠውየው ስለ ገንዘብ እና አጠቃቀሙ ያለው እስተሳሰብ እንጂ ገንዘብ ከመጠቀሚያነት ያለፈ ሀይል ያለው ነገር ሆኖ አይደለም በዚህ ድራማ ደሞ ገንዘብ ልብ ያለው በሁሉም መንገድ ላይ የሚሰራ ልክ የሞላው የህይወት ልክ ሆኗል ። ከባሏ ሞት በኋላ እራሷን የገንዘብ አምልኮ ውስጥ ያገኘችው መልከኛዋ ሃረግ በሃሳብ መንጎድ በዘመኑ ልክ መራመድ በህሊና መንቀሳቀስ ከብዷት በፍቅረ ነዋይ ሰክራ ትገኛለች በቀጣይ ምን ይፈጠር ይሆን ድራማው መልስ አለው ።
