abol tv logo

የጉዞ ምርጫዎ ስለ እርስዎ ምን ይናገራል?

ዜና14 ማርች 2026
በ"Out N' About" ፕሮግራማችን ኢትዮጵያን ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ስንቃኝ ሰንብተናል። ነገር ግን ሁሉም ሰው የሚወደው የጉዞ ዓይነት ይለያያል። የእርስዎ ተወዳጅ የጉዞ ቦታ ስለ ማንነትዎ ምን እንደሚናገር ያውቃሉ? እስቲ ራስዎን ይፈልጉ፦
Out And About Social Article

በ"Out N' About" ፕሮግራማችን ኢትዮጵያን ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ስንቃኝ ሰንብተናል። ነገር ግን ሁሉም ሰው የሚወደው የጉዞ ዓይነት ይለያያል። የእርስዎ ተወዳጅ የጉዞ ቦታ ስለ ማንነትዎ ምን እንደሚናገር ያውቃሉ? እስቲ ራስዎን ይፈልጉ፦

የሐረር ወዳጆች፦ የባህል እና የታሪክ አድናቂ!

የሐረር ንንብ እና ጠባብ መንገዶች ካማለሉዎት፣ እርስዎ የታሪካዊ ከተሞች ናፋቂ ነዎት። ከሰዎች ጋር መቀላቀል እና "ታሪክ ምንድነው?" ብሎ መጠየቅ ደስ ይለዎታል። እንዲያውም እርስዎ ሐረር ሄደው ከጅቦች ጋር ስጋ ሳይጋሩ የሚመለሱ ሰው አይደሉም። አዳዲስ ሰዎችን ማውራትና ወግ መጋራት ትልቅ ስጦታዎ ነው።

አንድነት ፓርክ እና ሙዚየሞች፦ ዝምተኛው ፈላስፋ!

በታሪክ ቅርሶች መካከል በዝምታ መዘዋወር የሚመርጡ ከሆነ፣ እርስዎ ፕሮፌሰር የመሆን አዝማሚያ አለዎት። ጫጫታ አይወዱም፤ ይልቅስ ጥንታዊ ነገሮችን እያዩ ማሰላሰልን ይመርጣሉ። በእግር ጉዞ ፋንታ የታሪክ መጽሐፍ የሚያክሉ ሙዚየሞችን ማየት ለእርስዎ ትልቅ እረፍት ነው።

የወንጪ ተጓዦች፦ ጭቃ አይፈሬዎቹ!

ወንጪን ከመረጡ፣ እርስዎ ተራራ ካልወጣሁ፣ ቁልቁለት ካልወረድኩ የሚሉ ፈረስ ግልቢያም ያማይጠሉ የጉዞ አፍቃሪ ነዎት። ትንሽ ጭቃና አድካሚ ዳገት ለእርስዎ እንደ ማሳጅ ነው። በጫማዎ ላይ ያለው ጭቃ ለሌላው ቆሻሻ ሊመስለው ይችላል፤ ለእርስዎ ግን የድል አድራጊነት ምልክትዎ ነው! "ተፈጥሮ ካለ እኔ አለሁ" ባይ ነዎት።

የሬስቶራንት ተመጋቢዎች፦ ፕሮፌሽናል ጉርሻ አዳኞች!

ለእርስዎ ጉዞ ማለት አዲስ ሜኑ ማየት ነው። ተራራ መውጣትና ምግብ መቅመስ ለእርስዎ እኩል ጀብዶች ናቸው። አዲስ ምግብ ቤት ተከፍቷል ከተባለ፣ አድራሻውን መጀመሪያ የሚያውቁት እርስዎ ነዎት። አዳዲስ ምግቦችን መሞከር የእረፍት ዋና የእረፍት ጊዜ ማሳለፊያዎ ነው!

ቢሾፍቱ እና ኩሪፍቱ ዋተር ፓርክ፦ አሳዎቹ!

ከውሃ ፓርክ ጨዋታዎች እና ከአስፈሪ ሸርተቴዎች መወርወር ካስደሰተዎት፣ እርስዎ የውስጥ ልጅነቱ ያልጠፋበት ተጫዋች ነዎት። መጮህ፣ መሳቅና ራስን በውሃ ውስጥ መዘፈቅ ለእርስዎ ምርጥ እረፍት ነው። "ኧረ ይሄ ያስፈራል!" የሚል ቃል በርስዎ መዝገበ-ቃላት ውስጥ የለም።

እስቲ እውነቱን እንነጋገር... የትኛው ይገልጻችኋል?

  •  የወንጪ ጭቃ አፍቃሪ?
  •  የሐረር ወግ አጥባቂ?
  •  የኩሪፍቱ አሳ?
  •  የአንድነት ፓርክ ፈላስፋ?
  • ወይስ የሬስቶራንት አዳኝ?

ምርጫችሁን በፌስቡክ ፖስቱ ኮሜንት ላይ አሳውቁን!

Out And About ዘወትር ዕረቡ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ እንዳያመልጥዎ!

የአቦል መዝናኛዎችን ለመከታተል ደምበኝነትዎን ያስቀጥሉ፡ https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6