ቃታ ድራማ ከአምስት ክፍሎች በኋላ፣ ታሪኩ እየረገበ ሳይሆን ይበልጥ እየተወሳሰበ እና የብዙዎችን ቀልብ እየገዛ ቀጥሏል። በመንደሩም ሆነ በዘራፊዎቹ መካከል የታዩት ክስተቶች ልባችንን አንጠልጥለውታል። የታሪኩን ሙቀት የጨመሩ አራት ዋና ዋና ጉዳዮችን እነሆ፦
1. አንለይ እና ትርሲት፦ የአሳዳጆች ጥብቅ ክትትል
አንለይ በዝርፊያው ወቅት በደረሰበት የጥይት ቁስል በሞት እና በሽረት መካከል ቢቆይም፣ በእጮኛው በትርስቲት ታማኝነት እና እንክብካቤ አገግሟል። ሆኖም እረፍት አላገኘም፤ የቡድኑ መሪ ያዬህራድአንለይን እንዲያድኑ የላካቸው መሳይ እና ጥሩነህ እንደ ጥላ እየተከተሉት ይገኛሉ። ትልቁ ድንጋጤ የተፈጠረው አኒሌ እና ትርሲት የሐሰት ፓስፖርት አሰርተው ለማምለጥ ሲሞክሩ እጅ ከፍንጅ በተያዙበት ወቅት ነው። አኒሌ በዚህ ጊዜስ ከአሳዳጆቹ ሊያመልጥ ይችል ይሆን?
2. የሉሊት ስቃይ እና የጫካው ፍጥጫ
በሉሊት ቤት ውስጥ ያለው ሰላም ሙሉ በሙሉ ደፍርሷል። ባለቤቷ ተኮላ የሚያደርስባት በደል እና ስቃይ ከመጠን ያለፈ ሆኗል። ሉሊት በበኩሏ ልጇ በድንገት በዘራፊዎች በተጣለ ሽጉጥ ጓደኛውን ዶዮን በጥይት መምታቱን ደብቃ ልጇን ለመከላከል ስትታገል ቆይታለች። ይሁን እንጂ ተኮላ ሉሊት ሽጉጡን መያዟን ደርሶባት በጫካ ውስጥ ሲያባርራት በነበረው ግብግብ ተኮላ በጥይት ተመትቷል። ለመሆኑ ተኮላን በእውነት ማን ማነው የተኮሰበት? ሉሊት ወይንስ ሌላ በጫካው ውስጥ የነበረ ሰው?
3. የመንደሩ የሥልጣን ሽኩቻ
በመንደሩ አስተዳዳሪነት ዙሪያ ያለው ጦርነት አዲስ መልክ ይዟል። የአሁኑ አስተዳዳሪ መኮንን በህዝቡ ዘንድ የተከበሩ ቢሆኑም፣ በሴራ የተሞላው ታሪኩ ግን ስልጣኑን ለመንጠቅ የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም። ታሪኩ "ከመኮንን የተሻለ እሰራለሁ" በሚል ስሜት የሚያስፋፋው የክፋት ሴራ አሁን ቀጥታ ወደ መኮንን እየመጣ ይገኛል።
4. ክህደት ያስከተለው ጥይት፦ የከተማ መመታት እና የዘምበላቸው ፍርድ!
ከተማ የዶዮ እናት ከሆነችው አያናለም ጋር የነበረው አላስፈላጊ ቅርበት መጨረሻው የከፋ ሆኗል። የአይናለም ባል ዘምበላቸው ጉዳዩን ደርሶበት በነበረው ግጭት ከተማ በጥይት ተመትቷል። ለዚህ ሁሉ ጠብ መባባስ ደግሞ እሳቱን ያቀጣጠለውና ለዘምበላቸው መረጃውን በመስጠት እንዲጋጩ ያደረገው ሴረኛው ታሪኩ ነው። አሁን ላይ ዘምበላቸው በፈጸመው ድርጊት በመንደሩ ፊት ቀርቦ የህግ ውሳኔ እየጠበቀ ይገኛል።
ታሪኩ የተከበሩትን አቶ መኮንንን ከስልጣናቸው ለማውረድ ያቀደው ተንኮል ይሳካለት ይሆን?
ቃታ ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ እንዳያመልጥዎ!
የአቦል መዝናኛዎችን ለመከታተል ደምበኝነትዎን ያስቀጥሉ፡ https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6



