channel logo
Bashager Home Page Billboard
channel logo

Bashager

465DramaPG13

አዲሱን "ባሻገር" ድራማ እንድንወደው ያደረጉን ነገሮች!

ዜና01 ኦክቶበር 2025
የአቦል ቲቪ አዲሱ ድራማ "ባሻገር" በኢትዮጵያ ተከታታይ ድራማ ዓለም ውስጥ ያልተለመደ እና አጓጊ የሆነ አዲስ አቀራረብ ይዞ መጥቷል።
Bashager Article cover

የአቦል ቲቪ አዲሱ ድራማ "ባሻገር" በኢትዮጵያ ተከታታይ ድራማ ዓለም ውስጥ ያልተለመደ እና አጓጊ የሆነ አዲስ አቀራረብ ይዞ መጥቷል። ይህ ድራማ ከተለመደው የታሪክ አካሄድ ባሻገር በመሄድ ተመልካቾችን ወደ ስሜት እና ምርምር ወደ ሚጠይቅ ውስብስብ ጉዞ ይወስዳቸዋል። እርስዎም “ባሻገር”ን ሊዎዱት የሚችሉበት ሦስት ዋና ምክንያቶች እነሆ!

1. የጊዜ መዛባት እና የትረካው ለየት ማለት"ባሻገር" የተለመደውን የትረካ ቅደም ተከተል በመተው በ8 አመታት ውስጥ ባለ ጊዜ ውስጥ ይተመላለሰ ይቀጥላይቀጥላል። ይህ ያልተለመደ የአተራረክ ዘይቤ ታሪኩን እጅግ በጣም ሚስጥራዊ ያደርገዋል። ዛሬ የምታዩት ክስተት ምንጩ ያለፈው ላይ ተደብቆ እና ነገ የምታዩት ደግሞ የዛሬ ውጤት ሆኖ ታገኙታላችሁ። ድራማው ተመልካች ስለታሪኩ እንዲገምት እና የታሪኩን ቁርጥራጮች ሰብስቦ እንዲረዳ ያስገድዳል።

2. የጀግናው የአካ ቦቹ ፈተና
አንድ መጥፎ አጋጣሚ  የትልቅ ፈተና ምክንያት ይሆናል። ይህ ታሪክ አንድ ንፁህ ሰው በፍትህ መጓደል ውስጥ ሲያልፍ የሚያሳየው ጥልቅ ስሜት ቀስቃሽ ፍልሚያ ብዙዎችን ያሳዝናል፣ ከገጸባህሪውም ጋር አብሮ አጓጊ ትግል ውስጥ ይከታል!

3. የህይወት ዕጣ ፈንታ እና የገጸ-ባህሪያት ጥልቀት
ድራማው የሰዎችን ውስጣዊ ጥንካሬ፣ መከራ እና የህይወት ለውጥ ያሳያል። በተለይም የአካ ቦቹ እና የኒሻን ታሪክ በሰዎች መካከል ያሉ ጥብቅ ግንኙነቶች እና አስቸጋሪ ጊዜያት የሰውን ልጅ እንዴት እንደሚለውጡ ያሳያል። እያንዳንዱ ገጸ-ባህሪ በራሱ መንገድ ለውጥ ያሳያል…. ከጊዜ፣ ከምክንያት፣ ከበደልና ከፍትህም ባሻገር ምን እንዳለ በጉጉት እንድንጠብቅ ያደርገናል።

ይህንን በአይነቱ ልዪ እና አጓጊ ድራማ "ባሻገር" ሰኞ ምሽት 2፡00 በአቦል ቲቪዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉ።

የአቦል ድራማዎች እንዳያመልጥዎ ደምበኝነትዎን ያስቀጥሉ፡ https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6