አንዳንዴ የልብ ጓደኛን የምናገኘው ካልጠበቅነው ቦታ ነው። በዚህ ወር ትኩረታችንን የሳቡት እና የእውነተኛ ጓደኝነት ትርጉምን ያስተማሩን ጓደኛሞች እነዚህ ናቸው፦
1. ኪያ እና ሊዲያ (ግዛት)፦ ከጠላትነት ወደ ታማኝ ወዳጅነት
የእነዚህ ሁለቱ ታሪክ "የማናየው የለም" የሚያሰኝ ነው። መጀመሪያ አካባቢ በየሄዱበት የሚጋጩ እና የማይስማሙ ቀንደኛ ጠላቶች ነበሩ። ሊዲያ የኪያ ግማሽ ወንድም የቀድሞ ፍቅረኛ በመሆኗ በመካከላቸው የነበረው ቅሬታ ቀላል አልነበረም። ነገር ግን ኪያ በሱስ እና በብቸኝነት ተስፋ በቆረጠችበት፣ ቤተሰቦቿም ጆሮ በነፈጓት ሰዓት ብቸኛ መሸሸጊያዋ የሆነችው ሊዲያ ናት። ሊዲያ ለኪያ ያሳየችው ርህራሄ የእውነተኛ ጓደኝነት ተምሳሌት አድርጓታል።
2. ኑሃሚን (ኒዮ) እና አይናለም (ግዛት)፦ የአክስት እና የወንድም ልጅ ልዩ ወዳጅነት
ምንም እንኳን አይናለም የኑሃሚን አክስት ብትሆንም፣ ግንኙነታቸው ግን ከቤተሰብ ዝምድና በላይ ነው። ኒዮ ምስጢሯን ሁሉ የምታካፍላት፣ የምትመካባት እና እንደ እኩያ ጓደኛዋ የምታያት አይናለምን ነው። በተለይ ደግሞ የኒዮ አባት (የአይናለም ወንድም) በሆነው በመርማሪ ተሾመ ላይ በጋራ የሚያብሩት እና የሚያሳዩት ፍቅር ማንኛዋም ወጣት ሴት የምትመኘው ዓይነት ግንኙነት ነው።
3. ሉሊት እና አይናለም (ቃታ)፦ በመከራ ቀን የጸና ወዳጅነት
አይናለም ለሉሊት ካለችው ታማኝነት በላይ ምን ሊኖር ይችላል? ሉሊት ከባለቤቷ ተኮላ የሚደርስባትን ግፍ እና ስቃይ በጽናት እንድትቋቋም አይናለም ትልቅ ደጋፊ ሆናታለች። ሆኖም አሁን ግንኙነታቸው ትልቅ ፈተና ውስጥ ወድቋል። የአይናለም ልጅ ዶዮ የሞተው በሉሊት ልጅ እጅ መሆኑ መታወቁ ለጓደኝነታቸው ትልቅ መፈተን ነው። ሉሊት አሁን ለአይናለም "አለት" መሆን ያለባት ጊዜ ቢሆንም፣ አይናለም እውነቱን ስታውቅ ግንኙነታቸው ምን ይሆን?
4. ምትኩ እና ሰመረ (ግዛት)፦ የምስጢረኞቹ ጥምረት
ምትኩ የሰመረ አጎት ቢሆንም፣ ግንኙነታቸው ግን ከአጎትና የወንድም ልጅነት የላቀ ነው። ሰመረ በቤቱ ውስጥ እንደ እንጀራ እናቱ ሐረግ ካሉ የቤተሰቡ አባላት ጋር የተወሳሰበ ግንኙነት ቢኖረውም፣ ብቸኛ አጋሩ እና የልብ ጓደኛው ምትኩ ነው። ምንም እንኳን ሁለቱም ሁሌ ለጥሩ ስራ ባይሰለፉም፣ በመካከላቸው ያለው መተማመን እና መደጋገፍ ግን በአስቸጋሪው የ"ግዛት" ቤት ውስጥ ብቸኛው ጽኑ መሰረት ሆኖላቸዋል።
የአቦል ቲቪ ጓደኛሞች ውጣ ውረዶች ቢቀጥሉም አብረው ይውጡታል💪።
በ #MyDStv መተግበሪያ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6
በ DStv Stream መተግበሪያ የሚወዱትን ድራማዎች ይከታተሉ

