በወይራዬ መንደር ውስጥ የሚጀምረውና በአንድ አጋጣሚ የብዙዎችን ህይወት የሚቀይረው የቃታ ታሪክ፣ በአቦል ቲቪ ሊቀርቡ ካሉ ተወዳጅ ድራማዎች መካከል አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል። ስለ ድራማው አጀማመር የወደድናቸውና በጉጉት እንድንጠብቀው ያረጉንን 4 ዋና ዋና ነጥቦች እነሆ።
1. በድርጊት እና በውጥረት የተሞላ ታሪክ
ድራማው በሰላማዊው የወይራዬ መንደር ውስጥ የሚፈጠርን አንድ ያልተጠበቀ ዘረፋ እና እሱን ተከትሎት የሚመጣውን የፖሊስ ፍልሚያ ተከትሎ ይነሳል። በአባሮሹ መሃል ከመኪና ላይ የወደቀ አንድ መሳሪያ በሁለት ህፃናት እጅ መግባቱ ደግሞ የመንደሩን ሰላም የሚያናጋ ትልቅ ክስተት እዲፈጠር ምክኛት ይሆናል። ድራማው ገና ከጅምሩ በፈጣን እንቅስቃሴ እና በልብ አንጠልጣይ ትዕይንቶች የተሞላ ነው።
2. የአንጋፋ እና የአዳዲስ ተዋንያን ጥምረት
በዚህ ድራማ ላይ በኢንዱስትሪው ውስጥ የሚታወቁ አንጋፋ ተዋንያን እና አዳዲስ ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች በሚያስደንቅ የትወና ብቃት ተጣምረው ቀርበዋል ። እንደ ተሾመ ታሴ (ጋጋ) ያሉ ተዋያን፣ በገጸ ባህሪያቱ መካከል የሚታየው መስተጋብር እና እያንዳንዱ ተዋናይ ለታሪኩ የሚሰጠው ህይወት፣ ድራማው እውነተኛ ስሜት እንዲፈጥር እና ተመልካችን የሚስብ እንዲሆን አድርጎታል።
3. ማህበራዊ ጉዳዮችን በጥበብ የሚዳስስ ይዘት
“ቃታ” ከድርጊት እና ከውጥረት ባለፈ፣ ጥልቅ የሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮችን በጥበብ ይዳስሳል ። ድራማው የሚከተሉትን ነጥቦች በታሪኩ ውስጥ ያካተተ ነው። የማንነት ፍለጋ፣ ማህበራዊ ግንዛቤ፣ ታማኝነት እና የጾታ ተጽእኖ አይነት ጉዳዮች በታሪኩ ውስጥ ይዳሰሳሉ።
4. በማይገመቱ ክስተቶች የተሞላ ማዕበል
ቃታ ዝም ብሎ የሚታይ ድራማ አይደለም፤ በየክፍሉ "ቀጥሎ ምን ይፈጠር ይሆን?" የሚያሰኝ አጓጊ ጉዞ ነው። በአንድ ትንሽ አጋጣሚ የጀመረው ግርግር ወደ ግዙፍ ሴራ እና ያልተጠበቁ ግጭቶች ሲያመራ ማየት ልዩ ስሜት ይፈጥራል። ታሪኩ የት እንደሚቆም እና ማን አሸናፊ እንደሚሆን መገመት አለመቻሉ፣ የቴሌቪዥን መስኮትዎ ላይ ተጣብቀው እንዲቀሩ ያደርግዎታል።
እናንተም ይህን ድንቅ ልብ አንጠልጣይ ድራማ ተጋበዙ!
ቃታ ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ እንዳያመልጥዎ!
የአቦል መዝናኛዎችን ለመከታተል ደምበኝነትዎን ያስቀጥሉ፡ https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6

