channel logo
Girid Showpage Billboard
channel logo

Girid

465DramaPG13

አዲሱን ግርድ ድራማ ጓግተን እንድናየው የሚያደረጉን 3 ነገሮች!

ዜና19 ሴፕቴምበር 2025
አቦል ቲቪ አዲስ እና ልብ አንጠልጣይ ድራማ ግርድን ይዞልን መጥቷል።
Girid Article poster

አቦል ቲቪ አዲስ እና ልብ አንጠልጣይ ድራማ ግርድን ይዞልን መጥቷል ። ይህ ታሪክ ከጓደኝነት፣ ከስልጣን እና ከበቀል ጋር በተያያዙ ውስብስብ ሴራዎች ላይ ያተኩራል ። “ግርድ” ተመልካቾችን ከማይጠበቅ ታሪክ እና በጥልቅ ከተፈጠሩ ገጸ-ባህሪያት ጋር ወደ አዲስ የዓለማት ስሜት ይወስዳቸዋል። የሚከተሉት ሶስት ነገሮች ደግሞ 

1. ምስጢራዊ እና አጓጊ የታሪክ መስመር

“ግርድ” ከአንድ ሚስጥራዊ የመንግስት የምርምር ፕሮጀክት ጋር የተያያዙ የቀድሞ ባልደረቦች ቡድን ታሪክ ይተርካል ። የፕሮጀክቱ ስኬት መሪዎቹ አፈወርቅ፣ ዘሪሁን እና ዮሴፍ ጓደኛቸውን አቤልን አሳልፈው እንዲሰጡት ምክንያት ሆኗል ። ከሃያ ዓመታት በኋላ፣ አቤል ለመበቀል ተመልሶ ሲመጣ፣ በጥንቃቄ የተገነቡ ህይወቶች መናወጥ ይጀምራሉ ። ይህ ታሪክ የያዘው ውስብስብ የፍቅር፣ የክህደት እና ያለፉ ክስተቶች ውጤቶችን ነው።

2. የማይረሱ ገጸ-ባህሪያት

በ”ግርድ” ውስጥ ያሉት ገጸ-ባህሪያት ህይወት ያላቸውና የእውነት የምናቃቸው ይመስላሉ። የአቤል ወደ በቀል መመለስ እና በሱ ዙርያ ያሉ ለተንኮል የሚዳርጉ ሁነቶች ምክንያት ለማወቅ የድራማው ተመልካቾች እንድናሰላስል ያደርጋሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የነጺዮን ጓደኝነት እና በግቢ ህይወት ውስጥ ሚገጥሟቸው ነገሮች የወጣትነት ይይወት ያስቃኙናል። ሁሉም ገፀ-ባህሪያት በውስብስብ ሴራ ውስጥ ተይዘው ተመልካቾች ማንን ማመን እንዳለባቸው እንዲጠራጠሩ ያደርጋሉ።
 


3. ከምስጢሮች እና ከሴራዎች በስተጀርባ ያለው እውነት

ከአቤል መመለስ ጋር፣ አዳዲስ ሚስጥሮች መጋለጥ ይጀምራሉ። የበርካታ ገጸ-ባህሪያት እውነተኛ ማንነት እና ያለፉት ድርጊቶቻቸው ይፋ ይሆናሉ። አቤል ፍትህን ለማግኘት በሄደበት መንገድ ላይ ስልጣን፣ ጥላቻ እና ፍቅር ይፋለማሉ። ይህ ድራማ መልስ በመፈለግ ላይ ያተኩራል። እኛም መልሱን እስክናገኝ ማየታችንን አናቆምም!

ይህ አስደናቂ ታሪክ ሲገለጥ ለመመልከት፣ “ግርድ”ን ዘወትር ማክሰኞ በአቦል ቲቪዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይከታተሉ።

የአቦል ድራማዎች እንዳያመልጥዎ ደምበኝነትዎን ያስቀጥሉ፡ https://mydstv-thiane.onelink.me/ivCe/qpuy2sa6