ፍቅር ለማግኘት አንድ ፎርሙላ የለውም። የጎጇችን ጥንዶች ያስተማሩን፣ ፍቅር በማይጠበቅበት ቦታ እና ባልታሰበ መንገድ መገኘት እንደሚችል ነው። እርስዎ ስለትዳር እና እውነተኛ ፍቅር አልመው የሚያውቁ ከሆነ እነዚህን ልብ የሚነኩ ታሪኮች ያንብቡ!
በስራ ላይ የተጀመረ ፍቅር
ማንኛችንም የትኛው አጋጣሚ ህይወታችንን እንደሚቀይር ልንገምት አንችልም። ፍሬሕይወትም ከፍሬዘር ጋር መስራት ስትጀምር የወደፊት ባልዋን እንዳገኘች አላወቀችም ነበር። ነገር ግን የፍቅር ጥያቄ ከፍሬዘር ሲመጣ እሷ ፍቃደኛ ሆና ተቀብላዋለች። ይህ የሚያሳየን የፍቅር ህይወት የት እንደሚጀምር ማወቅ እንደማንችል ነው። ስለዚህ እነዚህ አጋጣሚዎች ሲመጡ ልብዎን ከፍተው እንዲጠብቁ እንመክርዎታለን።
የፍሬዘር እና ፍሬሕይወትን ሰርግ ይመልከቱ፡
በትምህርት ቤት የተገኘ ፍቅር
አወቀ የመጨረሻ አመት ተማሪ በነበረበት ወቅት መስታወት የመጀመሪያ አመት ዩንቨርሲቲ ትምህርቷን ጀመረች። በእህት እና ወንድምነት የዘለቀው የአወቀ እና መስታወት ግንኙነት ከመስታወት ዩንቨርሲቲ ምረቃ በኋላ ወደ ፍቅር ግንኙነት ተሻግሯል። ይህ የሚያስተምረን እውነተኛ ፍቅር ትዕግስት እና ጊዜ እንደሚያስፈልገው ነው! እርስዎ ፍቅርን በትዕግስት እየጠበቁት ነው?
የአወቀ እና መስታወትን ጋብቻ ይመልከቱ፡
የልጅነት እና አብሮአደግ ፍቅር
ኢብራሂም እና ዘሃራ የተዋወቁት ኢብራሂም የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ እና ዘሃራ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለች ነበር። ኢብራሂም ዘሃራን በመጀመርያ ደረጃ በአይን ፍቅር ነበር የወደዳት። ከተዋወቁ ከትንሽ ጊዜ በኋላ እጮኛው አደረጋት። ይሄ የሚያሳየን የልጅነት ፍቅር አድጎ ለትዳር መብቃት እንደሚችል ነው። እርስዎ በልጅነትዎ ካፈቀሩት ሰው ጋር ለጋብቻ በቅተዋል?
የኢብራሂም እና ዘሃራን ሰርግ ይመልከቱ፡
እነዚህ አስደሳች የፍቅር ታሪኮች ፍቅርን በተስፋ እንድንጠብቅ ያደርጉናል። እርስዎ ከፍቅር አጋርዎት ጋር እንዴት ተዋወቁ? በማህበራዊ ሚዲያ ገጻችን ላይ ኮሜንት በማድረግ ያሳውቁን! ሌሎች አስደሳች የፍቅር ታሪኮችን በጎጇችን ዘወትር አርብ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ዱካ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 466 ይከታተሉ!