Logo

የባስሊቆስ ዕንባ - በጉጉት እየተጠበቀ የነበረው ድራማ!

ዜና
08 ኦገስት 2023
የባስሊቆስ ዕንባ በአቦል ዱካ አርብ ሐምሌ 28 ጀምሯል።
yebasilikos enba first article

በመጀመሪያ መጽሃፍ የነበረው የባስሊቆስ ዕንባ ወደ ተከታታይ ድራማ ተቀይሮ በአቦል ዱካ እየቀረበ ይገኛል።

ሁሉም ሰው እርስ በራስ የሚተዋወቅበት ዳባት የምትባል ትንሽ ከተማ አለ። ብርሃን የተባለች አንዲት ወጣት ሴት አዲስ አመትን ከቤተሰቧ እና ለብዙ አመታት አግኝታው የማታውቀው የልጅነት ፍቅረኛዋ ጋር ለማሳለፍ፣ ከኮሌጅ ትመጣለች።

ይህ አስደሳች ታሪክ ብርሃን ከልጅነት ፍቅረኛዋ ጋር ለመታረቅ ስትሞክር የምታሳልፋቸው ልዪ ልዪ ጊዜያት እና አስገራሚ አጋጣሚዎችን ያቀርባል። ይሄን አስደሳች የፍቅር ታሪክ ዘወትር አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ዱካ መከታተል ይችላሉ።

እርስዎ ከመጀመሪያው ክፍል የወደዱት ምንድን ነበር? የብርሃንን ታሪክ ለመመልከት በጉጉት እየተጠባበቁ ነው?

በማህበራዊ ሚዲያ ገጻችን ኮሜንት በማድረግ ያሳውቁን!