abol tv logo

የዲኤስቲቪ አዲሱ አቅርቦት አቦል ቲቪ

ዜና
24 ማርች 2021
የአዲሱ ቻናል አቦል ቲቪ አቅርቦቶች ይሄን ይመስላሉ።

የኤምኔት አዲሱ አቅርቦት አቦል ቲቪ ወደ ዲኤስቲቪ ክምችት ሊገባ ነው። ይህ ማስተላለፊያ ልዩ እና ሆን ተብሎ ለኢትዮጵያዊ አማርኛ ተናጋሪ ታዳሚዎች የሚቀርብ ነው። ብዙ ሚሊዮን ኢንቨስትመንት በምስራቅ አፍሪካ ባሉት ክልሎች ይዘትን በማሽያ ማጂክ ቦንጎ (ታንዛንያ)፣ ማሽያ ማጂክ ምስራቅ (ኬንያ)፣ ማሺያ ማጂክ ፕላስ (ኬንያ)፣ ፐርል ማጂክ (ዩጋንዳ)፣ እና ፐርል ማጂክ ፕራይም (ዩጋንዳ)፣ ያቀረበውን ምርት ኤምኔት በአዲሱ አስደሳች ማስተላለፊያ አቦል ቲቪን ለማካተት አሻራውን አስፍቶል።

በዚህ ማስተላለፊያ ውስጥ ታዳሚ የሚፈልገው ሁሉ ይካተታል፣ ከእውነታ ቲቪ እስከ ተከታታይ ድራማ፣ የህጻናት መዝናኛ፣ ዘፈን እና ሌሎችም ይገኙበታል። አቦል ቲቪ በዲኤስቲቪ መድረክ ማስተላለፊያ ቁጥር 146 ላይ ብቻ የሚገኝ ይሆናል።

እንደነዚህ አይነት ትርዒቶችን በጉጉት መጠበቅ ይችላሉ፤

አደይ

ከ አንዲት 17 አመት ልጃገረድ ጋር የተሳሰረውን የሁለት ቤተሰብ ሒወት እና ጉዞን የሚከተል ድራማ ነው። በዚህ ድራማ ውስጥ የሚቀርቡት ገጽታዎች ስለ ቤተሰብ፣ ጓደኝነት፣ ስሜት፣ ሃቅ፣ ታማኝነት፣ የአገር በቀል እውቀት፣ ጥበብ እና ከምንም በላይ ግን ፍቅር ነው። የዚህ ድራማ ትልቁ ተጨባጭነት ስለፍቅር ነው።

ጎጆአችን

ይህ ትርዒት የተሰራው ስለኢትዮጵያን ባሕል እና ቅርጽ በህብረት ውስጥ ያለውን ውበት ለማሰየት ነው። በትዳር እና ሕይወትን በመገንባት ውስጥ ያሉትን ተቀያያሪ አጋጣሚዎች ያሳያል። ከዚም በላይ፣ ይህ ሂደት የሃገሪቱን ማራኪ ቦታዎችን፣ የሙሽሮችን ዝግጅት፣ የህብረተሰቡን አኗኗርን፣ ልምድ እና የሃገሪቱን ስርዓት ያሳያል።

ስቱዲዮ 30

የዚህ እውነተኛ ተከታታይ ትርዒት ግብ፣ በአንድ ህንጻ ውስጥ ለመቅዳት ዝግጁ የሆነ ፕሮዱዩሰር እና መሳርያ ጋር የተለያዮ አርቲስቶችን አገናኝቶ በ 30 ቀን ውስጥ የሙዚቃ አልበም እንዲያቀናጁ ማድርግ ነው። የእውነተኛ ሒወትን ሂደት የሚከተል ሲሆን፣ የአልበም አሰራር ሂደትን፣ የመቅጃ ሳዓታትን እና ጥያቄ እና መልስ ከዘፋኞች እና ፕሮዱዩሰሮች ጋር በማሀል ያካትታል።

በቅርብ የሚጀምሩ

ዙረት

አንድ የወንጀል ድርጅት ከሃገሪትዋ በህግወጥ መንገድ ሚልየን ዶላሮችን ለማውጣት ይጥራሉ። ይሄንን ለማከናዎን ወደ ኢትዮጵያ የመጣውን መሪ ለመያዝ አንድ የፖሊስ ሰላይ እራሱን ሹፌር አስመስሎ ድርጅታቸው ውስጥ ይገባል። ነገር ግን፣ ሰላዮ ከድሮ ጀምሮ የሚያፈቅራት ልጅ የመሪው እጮኛ መሆንዋን ሲረዳ፣ ተልእኮውን ያወሳስበዋል።

ናፍቆት

ገላ፣ ግበዝ ዘፋኝ ብትሆንም በልጅነቷ ነው ልጅዋ አብቃልን የወለደችው። አብቃል ያደገው አባቱን ሳያቅ ነው፤ ግን ከእናቱ ጋር የሚጋራው የዘፈን ፍቅር እና ችሎታ ጠንካራ ግንኙነት ሰቷቸዋል። በልጅነቱ አብቃል እናቱን እህት እና ወንድም እንድትሰጠው ይጨቀጭቃታል። ስለዚህም ገላ እንደነሱ የመዝፈን ፍቅር ያላቸው ሁለት ሴት እና ወንድ ልጆችን ከጉዲፈቻ ወስዳ አብራ ማሳደግ ትጀምራለች። አብቃል በደስታ ያድጋል፣ ግን ቀስ በቀስ ከአንድዋ እህቱ ጋር በፍቅር ይወድቃሉ። ይህንን ግን እናቱ፣ ወንድሞችዉ እና እህቱ ይቃወሙታል።