Logo

በዚህ ሳምንት የምንሰናበታቸው ተወዳጅ የአቦል ቲቪ ድራማዎች!

ዜና
26 ጁን 2023
ፖዝ፣ አጋፋሪ ፣ ሳሎኑ እና ስውር በመጨረሻ የምንጠብቃቸው ነገሮች።
finale week shows - article

በይዘታቸው የሚለዩት አራት የአቦል ቲቪ አቅርቦቶች እያዝናኑ እና እያጫወቱን ቆይተዋል። ፖዝ በፎቶግራፊ ውድድር፣ አጋፋሪ ሳታየር፣ ሳሎኑ በኮሜዲ እና ስውር ቤተሰባዊ ድራማ የሰፈሩ ታሪኮች ነበሩ። የተመልካችን ልብ አንጠልጥለው የቆዩት ድራማዎች በዚህ ሳምንት መጠናቀቃቸውን አስመልክተን ምርጥ አፍታዎችን እንመልከት።

አጋፋሪ ምዕራፍ 2

የአጋፋሪ እና ጥንቅሹ ጥምረት፤ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ የሚያርፉት አስክሬኖች ከአጋፋሪ ጋር በመንፈስ በመወያየት ልዩ ልዩ የህይወት ታሪኮችን ተመልክተናል። ይሄንን ም ዕራፍ ልዩ ያደረገው ደግሞ የአጋፋሪ ችሎታ መንስኤ ማወቅ መቻላችን ነበረ። ከዚህም አልፎ አጋፋሪ ምዕራፍ 2 የዋና ገጸ ባህሪያት ጥንቅሹ እና አጋፋሪን ማንነት እና አስተሳሰብ ይበልጥ እንድንረዳ አድርጎናል። በተጨማሪም በአጋፋሪ የቀረቡ እንግዶች ታሪክ ሀሳብ እና ስሜትን የሚቀሰቅስ ነበረ።

እርስዎ ከአጋፋሪ የወደዱት ታሪክ ምን ነበር?

ከዚህ ቀደም በአጋፋሪ፡

ሳሎኑ ምዕራፍ 1

መላው አለም የውበት ሳሎን እና የሰፈር ታሪኮች እጅ ለጅ ነው የሚሄዱት። የኤልሳ ሳሎንም ይሄን ደንብ ተከትሎ ከጸጉር ማስተካከል አልፎ ማህበራዊ ጉዳዮችን እያዝናና እና እያሳሳቀ ያቀርብልናል። ሳሎኑ የተለያዩ ግለሰቦችን የለት ተለት አኗኗር እና ደምብን በአስቂኝ መንገድ ሲያስቃኘን ቆይቷል። በዚህ ኮሜዲ ድራማ ላይ ከቀረቡት ገጸ ባህሪያት የትኛው አዝናንቶት ነበር?

ከዚህ ቀደም በሳሎኑ፡

ስውር ምዕራፍ 1

ለእራሷ እና ለሶስት ሴት ልጆቿ የተሳካ አለም ለመገንባት የምትጥር ሴት እና የሚያጋጥሟትን ፈተና ያስቃኘናል። ስንዱ የልጆቿ ህይወት ለማሻሻል የምታደርገው ጥረት ከፍላጎታቸው ጋር እየተጋጨ ነገሮችን ያወሳስባል። ስንዱ ለልጆቿ ስትል ያደረገቻቸው ነገሮች ሁሌም ትክክል ባይሆኑም የእናትነቷን ፍቅር ያሳይ ነበር። ስንዱ ከቤት ውጪ የሚመጡትን ጥቃቶች ስትከላከል ልጆቿ በሚወዷቸው ባለቤቶቻቸው በመበደላቸው ከእናታቸው ጋር መስማማት አቅቷቸው ነበር። እርስዎ ስለ ስውር ድራማ የወደዱት ምንድን ነበር?

ከዚህ ቀደም በስውር፡

ፖዝ ምዕራፍ 2

በፎቶግራፍ ጥበብ ላይ ያተኮረው ፖዝ የፎቶግራፍ ባለሞያዎች ውድድር፣ የተወዳዳሪዎችን አስገራሚ ችሎታ የታየበትና ፉክክሩ ጠንክሮ የቀረበበት ነበር። በዚህም አስደናቂ ውድድር ላይ ፎቶግራፈሮች ልዩ አይነት ፈተና ቀርቦላቸው ነበረ፣ ለምሳሌ ውሻዎችን ፎቶ በማንሳት፣ የቅርጫት ኳስ ጨዋታን ፎቶ ማንሳት እናም የተለያዩ መጠጦችን ፎቶ በማንሳት ተወዳድረው ነበር። ከዚህ አልፈው የቀሩት ሁለት ተወዳዳሪዎች ደግሞ በዚህ ሳምንት ውጤታቸው ይጋለጣል:: እርስዎ ማን ያሸንፋል ብለው ያምናሉ?

ከዚህ ቀደም በፖዝ፡

በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ሁሉም አለ! እርስዎ በጉጉት ሲከታተሉ የነበረውን ድራማ በማህበራዊ ሚዲያዎች ኮሜንት ያድርጉ!