Logo
Derash S1
channel logo

Derash

465DramaPG13

የደራሽ ገጸ ባህሪያት ምስጢሮች።

ዜና
25 ሜይ 2023
እያስገረሙን የሚገኙ በደራሽ የተጋለጡ ምስጢሮች።
Derash article secrets

ደራሽ የሁለት ቤተሰብን ትስስር እና የህይወት ታሪክ የሚያስቃኝ ድራማ ነው። በርግጥ የደራሽ ገጸ ባህሪያት ብዙ ውጣውረድ አሳልፈዋል፣ የግድያ ወንጀል፣ የመኪና ስርቆት ወንጀል፣ ድብቅ ቤተሰባዊነት እና ሌሎች የተለያዩ ችግሮች ገጥሟቸው ነበር። በአሁ ሰዓት ደግሞ የደራሽ ገጸ ባህሪያት እነዚህ ምስጢሮች እንዳይደረሱባቸው ለመደበቅ ይሞክራሉ።

የምስጋና ምስጢር

የምስጋና ህይወት የተቀየረው በአንድ ምሽት ላይ በተከሰተ ነገር ነው። ደሊናን ለማስደሰት ብሎ የተሳተፈበት መኪና ስርቆት ባልጠበቀው ሁኔታ የሰው ገዳይ አድርጎታል። ምስጋና ይሄን እውነት ከቤተሰቡ እና ፖሊሶች ለመደበቅ የሚያደርገው ጥረት ይበልጥ ያልጠበቀው አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል። የምስጋናን ሚስጥር ማን የሚደርስበት ይመስልዎታል?

የምስጋናን ህይወት የቀየረውን ምሽት ይመልከቱ፡

የጋሽ ዝናው ምስጢር

የጋሽ ዝናው ሞያ አስፈሪ እና ህገወጡ የመኪና ስርቆት ስራ ነው። በዚህም ሞያ ውስጥ ብዙ ሰዎችን ለጥቅሙ ብሎ ይጎዳል፣ ከእነዚህም አንዱ የልጁ ባለቤት ጌታቸው ነው። ጋሽ ዝናው የጌታቸው ግድያ ላይ እጁ እንዳለ ከብሌን መደበቅ አልቻለም ነገር ግን የገዳዩን ማንነት መደበቅ ችሏል። ብሌን ባሏን የገደለው የድሮ ፍቅረኛዋ ልጅ መሆኑን ካወቀች ምን ታደርግ ይሆን? ጋሽ ጌታቸው እውነቱን ለመደበቅ ምን አይነት እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል አይታዋቅም።

ብሌን በባለቤቷ ግድያ ላይ የአባቷ እጅ መኖሩን ስታውቅ ምን እንዳደረገች ይመልከቱ፡

የብሌን ምስጢር

ብሌን፣ ጌታቸውን አግብታ ሌላ ሰፈር መኖር ከጀመረች በኋላ የድሮ ህይወቷን እርግፍ አድርጋ ትታው ነበር። የባሌቤቷ ግድያ ወደ ጋሽ ዝናው ቤት መልሶ ሲያመጣት ግን፣ ብዙ የረሳችው እና የደበቀችው እውነቶች ተጋልጠዋል። ከእነዚህ ድብቅ እውነቶች አንዱ፣ የትልቁ ልጇ የልኡል አባት ማንነት ነው። ህይወቱን ሙሉ አባቱ ጌታቸው መሆኑን ያመነው ልኡል ከድሮ ፍቅረኛዋ መላኩ ጋር መቀራረብ ሲጀምር ምስጢሯ ይጋለጣል ብላ በማመን ሁለቱን ለማለየያየት ትሞክራለች። ብሌን ይሄንን ከባድ ምስጢር ለምን ያህል ጊዜ መደበቅ ትችል ይሆን? ልኡል ይሄን እውነት ካወቀ ይቅር የሚላት ይመስልዎታል?

ብሌን መላኩ እና ልኡልን ለማለያየት የምታደርገው ጥረት ይሄን ይመስላል፡

የገሊላ ምስጢር

ገሊላ በመላኩ እና ብሌን መካከል ያለውን ታሪክ ሁሌም ትጠላው ነበር። አሁን ደግሞ በተጨማሪ የብሌን እና መላኩን ታሪክ የሚያስቀጥል ነገር ተጋልጧል እናም ገሊላን በጣም እየረበሻት ነው። ገሊላ ይሄንን ምስጢር ሰምታ፣ መላኩ መቼም እንዳያውቀው ለማድረግ መርጣለች። እርስዎ በእሷ ቦታ ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?

ገሊላ የምታውቀውን ምስጢር ለመደበቅ የምታደርገው ጥረት ይሄን ይመስላል፡

የደራሽ ገጸ ባህሪዎች ሁሌም ልባችንን የሚያንጠለጥል ድርጊቶችን በማድረግ በድራማው መስጠውናል። እርስዎ የትኛው ምስጢር ነበር ያስገረምዎ?

ደራሽ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!