አቦል ቲቪ በሚያዝያ ወር ላይ ተመልካቾችን በሚያስደስትና በሚመሰጥ መልኩ በተለያየ አይነት አቀራረብ ኣዳዲስ ይዘቶች ይዞ መጥቷል። ሁሉም አይነት ይዘት በአቦል ቲቪ አለ፦ ሰስፔንስ፣ ሳታየር፣ ፍቅር፣ ኮሜዲ እና ውድድር።
እንደ አንድ
በእናትነቷ እና ለቃልዋ በመታመን ማሃል ፈተና ውስጥ የገባች እናት ትንቅንቅ ያስቃኛል። ፍቅርተ የተቸገረውን ህዝብ ለመርዳት አስባ ሚስጢራዊ ቡድን መቀላቀሏ ከቤተሰቧ ተደብቃ ሚስጢራዊ ህይወት እንድትኖር ያስገድዳታል።
እንደ አንድ ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል። አዎ በትክክል አንብበውታል፣ ከሰኞ - አርብ በአቦል ቲቪ ብቻ!
አጋፋሪ ምዕራፍ 2
በህይወት እና በሞት መሀል ባለው ድልድይ ላይ ያልተቋጩ ጉዳዮችን የሚያስቃኘው በይዘቱ ለየት ያለው አጋፋሪ ምዕራፍ 2 ተከታታይ ድራማ ጀምሯል። በአዲሱ የአጋፋሪ ምዕራፍ ስለ አጋፋሪ ችሎታ ምንጭ ይበልጥ ታውቆ ስሜት የሚቀሰቅሱ ታሪኮች ይቀርባሉ።
አጋፋሪ ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል!
ስዉር
ለእራሷ እና ለሶስት ሴት ልጆቿ የተሳካ አለም ለመገንባት የምትጥር ሴት እና የሚያጋጥሟትን ፈተና ያስቃኘናል። ስንዱ የልጆቿ ህይወት ለማሻሻል የምታደርገው ጥረት ከፍላጎታቸው ጋር እየተጋጨ ነገሮችን ያወሳስባል።
ስዉር ዘወትር እሮብ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል!
ሳሎኑ
በርካታ ማህበራዊ ጉዳዮችን በሳቅ እና በለዛ እያዋዛ የሚያቀርብ አዲስ ተከታታይ ድራማ ነው። ከተለያየ የህይወት ጉዞ የመጡ የጸጉር ቤት ሰራተኞች ሳሎኑ ላይ ተግባብተው ስራቸውን ለማስፈጸም ይሞክራሉ።
ሳሎኑ ዘወትር እሮብ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል!
ፖዝ
በፎቶግራፍ ጥበብ ላይ ያተኮረው ፖዝ፣ የፎቶግራፍ ባለሞያዎች ውድድር የተወዳዳሪዎችን አስገራሚ ችሎታዎች እየታየበትና ፉክክርም እየጠነከረ መጥቷል። የፎቶግራፈሮችን አለም እና ስጦታ አቅርቦ የሚያሳይ ውድድር።
ፖዝ ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል!
አቦል ሚሊየነር ምዕራፍ 2
ይበልጥ በጠነከረ ፉክክር በምዕራፍ 2 ተመልሷል። አዲስ ዙር እና አዲስ ተወዳዳሪዎች! የዚህን ምዕራፍ አንድ ሚሊየን ብር ማን ያሸንፈው ይሆን?
አቦል ሚሊየነር አርብ ሚያዝያ 20 ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይጀምራል!
የማይረሱ በርካታ አዝናኝ አቅርቦቶች በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ብቻ ይቀርባሉ!