Logo

የሮዛ ሚስጥር ተጋልጧል - ባሻ ይሁን

ዜና
17 ኖቬምበር 2021
ሮዛ አባቷን ከእውነቱ ለመከላከል ሞክራለች።

ባሻ ይሁን ምዕራፍ 1 በልብ አንጠልጥይ መንገድ ተቋጭቷል። ባሻ ሮዛ በመጥፋትዋ ምክንያት እጅግ ተጨንቆ ታሟል:: ሮዛ ከትዳር ውጪ በማርገዟ አፍራለች። ባሻን ማዋረድ ባለመፈለጓ ከቤት ጠፍታለች።

የሮዛ ሚስጥር በፋናዬ፣ ቦሰኔ እና ማርታ ተደብቆ ቆይቷል። ግን በፋናዬ እና ማርታ መሀከል በተደጋጋሚ የሚፈጠረው ግጭት የሮዛን ሚስጥር ያጋልጣል። 

የባሻ ጤና ምን ይሆናል?

ሮዛ እውነቱ ስለተጋለጠ ወደ ቤቷ ትመለስ ይሆን? የማርታ እቅድ ምን ይመስለዎታል?

የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ለማወቅ የሚቀጥለው የባሻ ይሁን ምዕራፍ ይከታተሉ!