Logo

አዲሱ የአቦል ቲቪ ድራማ የተገፉት የመጀመሪያ እይታ - የተገፉት

ዜና
20 ኦክቶበር 2021
የመጀመሪያው ክፍል።

የተገፉት ድራማ ጥቅምት 10 ረቡዕ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ጀምሯል። ይህ በሰስፔንስ የተሞላ ድራማ የሁለት ቤተሰብ ጥምረት ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ ድራማው የተለያዩ ዘውጎችን ይዞ ቀርቧል።

ሊንዳ የህግ ባለሞያ ቢሮ ቃለመጠይቅ ለማድረግ ትዘጋጃለች። በዚህ ቢሮ ስራ በማግኘት እናቷ ሩሀማን ከነርስ ስራዋ እረፍት ለመስጠት እና ታናሽ ወንድሟን በስፔሻሊስት ለማሳከም ታልማለች።

ላምሮት ከምትወደው እጮኛዋ እና የልጇ አባት ጴጥሮስ ጋር ቀለበት ለማሰር ትዘጋጃለች። የጴጥሮስ የመጀመሪያ ሚስት ፌኔት ወደ ሆስፒታል ከመሄዷ በፊት ቤታቸው በማረፏ በጥንዶቹ መሀል ጸብ ይፈጥራል።

በዝግጅቱ መሀል ፌኔት የምትፈጥረው ግርግር ላምሮትን ያሳፍራታል። በፌኔት እና ላምሮት መሀከል በተፈጠረው ጥል ፌኔት ህይወቷ አለፈ ።

ለዚህ ድርጊት የፌኔት ነርስ ሩሀማ በመወቀሷ የቤተሰቧን ሕይወት ያጎሳቁላል። እነዚህ ሁለት ቤተሰቦች ወደፊት ምን ይጠብቃቸው ይሆን? ከበቀል እና ከህግ የትኛው ያሸንፋል?

ስለመጀመሪያው የተገፉት ክፍል ምን እንደተሰማዎት ያሳውቁን!

የተገፉት ዘወትር ረቡዕ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!