abol tv logo

የተገፉት ፡ የድራማው ይዘት

ዜና
13 ኦክቶበር 2021
የአቦል ቲቪ አዲሱ ድራማ።

አቦል ቲቪ ለውድ ተመልካቾቹ አዲስ ልብ አንጠልጣይ ድራማ ይዞ ቀርቧል።

የጤና ሚኒስቴሩ አቶ ጴጥሮስ እና ሚስቱ ላምሮት የመጀመሪያ ሚስቱ ፌኔትን ለመግደል ያቅዳሉ። ለፌኔት የተቀጠረችውን ነርስ ሩሃማን ገዳይ አስመስለው ከህግ ያመልጣሉ።

ሩሃማን አሳስረው ኑሯቸውን በነፃነት ሲቀጥሉ ስለግድያው እውነቱን የምታውቀው የጎረቤት ሰራተኛ ማርዬ ታስፈራራቸዋለች።

በኢኮኖሚ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ማህበረሰብ መካከል የሚፈጠሩ አስገራሚ ክስተቶችን ወይም ድርጊቶችን የሚያስቃኘን ድራማ ነው። ድራማው አንድ ታዋቂ ቤተሰብ ውስጥ በተፈጠረ ወንጀል ምክንያት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቤተሰቦች እንዴት እንደሚጎዱ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። 

የተገፉት ምዕራፍ 1 ቅምሻ

አቦል ቲቪ የተገፉት የተሰኘ አዲስ ድራማ ይዞ ይቀርባል! የተገፉት ረቡዕ ጥቅምት 10 ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ይጀምራል።? https://bit.ly/3BBL0yU #አቦልቲቪ #አቦል #የተገፉት

Posted by Abol TV on Wednesday, 13 October 2021

የተገፉት ጥቅምት 10 ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ይጀምራል። ስለድራማው ያለዎትን አስተያየት ኮመንት በማድረግ ያሳውቁን!