Logo

የባሻ ይሁን አስገራሚ አጀማመር - ባሻ ይሁን

ዜና
01 ሴፕቴምበር 2021
ስለባሻ ይሁን የመጀመሪያ ክፍል።

ባሻ ከቤት ሰራተኛቸው በጀመሩት ፍቅር እና በግቢያቸው ውስጥ ያሉ ሴቶች በአንድ ወንድ ምክንያት የገቡበት የፍቅር ጣጣ ወዴት ያመራ ይሆን?

ባሻ ይሁን አዲሱ የአቦል ቲቪ ኮሜዲ ድራማ ሲሆን ድራማው ባሻ የተባለ ችግር የማያጣው ሰው እና ከልጆቹ፣ የቤት ሰራተኞቹ እና ጎረቤቶቹ ጋር ያለውን የተለያየ ግንኙነት ይሳያል። የትዕይንቱ አስቂኝ ክፍል ሲጀምር ባሻ ፍርድ ቤት ለመሄድ ሲሞክር የጊቢው ሰው እንዳይሄድ ሲለምነው እናያለን።

ባሻ በሰፋሩ ስም ሰላማዊ ሰልፍ ለማቀናጀት እየሞከረ እንደሆነ እና የሰፈሩን ቆሻሻን ለማፀዳት እየተዘጋጁ ያሉት ከውጪ የመጡ ልጆች የሚያደርጉትን አያውቁም ብሎ ያስባል። በዚህ ምክንያት የተጀመረው ክርክር ጊቢው ውስጥ የተደበቁት ሚስጥሮች ብዙ መሆናቸውን እንረዳለን።

ባሻ ከቤት ሰራተኛው እሜቴ ፋኖስ ጋር ድብቅ ግንኙነት እለው በተጨማሪ ወሮ ፋኖስ ከባሻ ልጅ ሮዛ ጓደኛ እዮቤል ጋር ድብቅ ግንኙነት አላት። እዮቤል ድሞ ከሮዛ እና ጎረቤቱ ቢቲኮ ጋር ድብቅ ግንኙነት አለው።

ስለነዚህ የተሳሰሩ ግንኙነቶች ምን ያስባሉ? አስተያየትዎን አሳውቁን!

ባሻ ይሁን ማክሰኞ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይቀርባል!