Logo

ሶስት አስቂኝ ጊዜያት በአስኳላ

ዜና
10 ጁን 2021
በየኔታ እና በአስኳላ መምህራን መካከል ያለፉት በጣም አስቂኝ ጊዜዎችን እንመልከት፡፡

አስኳላ ሲትኮም የሚከተለው፣ መደበኛ ትምህርት ለመቀበል በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የገቡትን የ 43 ዓመት መምህር የኔታን ጉዞ ነው፡፡ የኔታ ላለፉት አራት ወራት በአስኳላ የመጀመሪያ ደረጃ  ትምህርት ቤት በአራተኛ ክፍል ተመዝግበዋል፣ ያሳለፉት ጊዜያትም በጣም አስቂኝ እና አስተማሪ ነበሩ። 

የኔታ እንደሌሎች ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለመማር ቢወስኑም፣ የአስተማሪዎቹ አካሄድ ሁሌም አልተዋጠላቸውም። የየኔታ የጥያቄ ማብዛት ባህሪ ከአስተማሪዎቹ ጋር በተለያዩ አጋጣሚዎች አስቂኝ ግንኙነት ሲፈጥር ተመልክተናል፡፡

በየኔታ እና አስተማሪዎቹ መካከል የመረጥናቸው ሶስት ምርጥ አስቂኝ አጋጣሚዎች እነዚህ ናቸው፡

       1. "የኔታ ፊደሎቹን አይውጡም"

በእንጊሊዘኛ ክፍለጊዜ ውስጥ ተማሪዎች ፊደላቸው የሚዋጡ ቃላቶችን ሲማሪ የኔታ ፊደሎቹ የሚዋጡ ከሆነ አስፈላጊ አይደሉም ብለው ከአስተማሪዋ ጋር የተከራከሩበት ጊዜ ነበር። ፊደሉን አልውጥም በማለታቸው፣ ክፍል ውስጥ አስቂኝ አጋጣሚ ተፈጥሯል።​​​

       2. "የየኔታ እርሻ ክፍል"

ትምህርት ቤት ተማሪዎቹን ስለ እርሻ እንደማይማሩ ሲረዱ፣ የኔታ የማስተማር ችሎታቸውን ተጠቅመው የእርሻ ክፍል ይጀምራሉ። አንድ ጠዋት የትምርቤቱ ዳይሬክተር የኔታ እርሻ ትምህርት ሲያስተምሩ ሲያገኟቸው ስለትምህርቱ ስለአስፈላጊነቱ ከየኔታ ጋር መከራከር ይጀምራሉ፣ የኔታ ለትምህርት እየተጠቀሙት የነበረውን ዶማም "የጦርነት መሳሪያ" ብለው ትምህርት ቤት ዶማው ደግሞ እንዳይመጣ ይከለክላሉ።

       3. "የየኔታ ሚስጥር ተልኮ"

የኔታ በአስኳላ  ያሉትን አንዳንድ “የተጋነኑ” ህጎች ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር በላቸው የኔታን መጠራጠር ይጀምራሉ፡፡ የኔታ ትምህርት ቤት የገቡት ሚስጥር ተልኮ እንዳለ እርግጠኛ በመሆን የአማርኛ እና ስዕል አስተማሪ ይነበብን እንዲረዳው በላቸው ያሳምነዋል። ይህ በላቸው ያመኑበት ተልዕኮ ብዙ አስቂኝ አጋጣሚዎች በአስኳላ ትምህርት ቤት ይፈጥራል።

እርስዎን በጣም ያሳቅዎት ምን እንደነበር ያሳውቁን!

አስኳላ እሮብ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 አንዳያመልጥዎ!