ማን ከ ማን የተሰኘ ፕሮግራም በአቦል ቲቪ ከዝነኛ እና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ጥልቅ ቃለመጠይቆችን እና በሙዚቃ ባንድ በሚደገፉ ድምፃውያን የቀጥታ የሙዚቃ ትርዒት ያቀርብልዎታል። ባለፈው ሳምንት ማን ከ ማን ላይ በመሳይ ተጋብዘው የነበሩት፣ ድምፃዊ ራሄል ጌቱ እና የኛ በተሰኘዉ ፕሮጀክት በቅርቡ እውቅና ያገኘቸዉ ቤቴልሄም ሸረፈዲን እና ተጋባዥ ድምፃዊ ኤልያስ ተሾመን ይዞ ቀርቧል።
ድምፃዊ ኤልያስ ተሾመ በቅርብ የተካሄድ የድምፃውያን ውድድር ላይ አንዱ ተፎካካሪ ነበር። በውድድር ስራዎቹ የሚታወቅበት የሚኒሊክ ወስናቸው “ትዝታ አያረጅም” የተሰኘውን ሙዚቃ እናም የራሱን አዲስ “ሆዴ” የተባለ ነጠላዜማ አቅርቧል።
ቤቴሌሄም የምትተውንበት ታዋቂው የኛ ስለተባለው በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ፕሮጀክት ታሳውቀናለች። የኛ ላይ የሚቀርቡት ተዋንያን ምን አይነት ውድድር እንዳደረጉ እና ቤቴልሄም እንዴት ከ1500 ተወዳዳሪዎች ጋር ተፎካክራ የ “ሃና” ገጸ ባህሪ እንደደረሳት አጫውታናለች። ለውድድሩ እስከ ሶስተኛ ዙር ሙከራ ስታደርግ ለአባቷ እንዳልተነገራቸው ገልፃለች። አባቷ የትወና እና ሙዚቃ ፍቅሯን ጠልተው ሳይሆን፣ ትወና ከመጀመሯ በፊት ትምህርቷን እንድታጠናቅቅ ይፈልጉ ነበር፣ ነገርግን የኛ ላይ ትወና መጀመሯን በደስታ ተቀብለውታል፡፡
ራሄል ጌቱ ከየኛ ተሳትፎዋ በኋላ ከተለያዩ ታዋቂ እና አንጋፋ አርቲስቶች ጋር አስቴር እና ጋሽ ማሃሙድ ጋር የሙዚቃ ስራዎችን ሰርታለች። ከዚህ በፊት ቤቴልሄም እና ራሄል በአካል ተገናኝተው ባያውቁም፣ ቤቴልሄም ከውድድሯ በፊት ለራሄል በስልክ ዘፈን አንጎራጉራላት ራሄል ውድድሩን ማለፏን እንደማትጠራጠር ነግራት ነበር።
በተጨማሪም ራሌል እና ቤቴልሄም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያላቸውን ታዋቂነት ተጠቅመው እንዴት የሀገሪቷን ጉዳይ እንደሚወያዩበት አሳውቀውናል።
በዚህ ማን ከ ማን ፕሮግራም ላይ ውድ ተመልካቾቻችን ያለዎትን አስተያየት ያሳውቁን።
ማን ከ ማንን ሀሙስ ከምሽቱ 3:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉት!