ታይተው የማይታወቁ ልብ አንጠልጣይ ድራማዎች፣ ኮሜዲዎች እና እውነተኛ የህይወት ታሪኮች በአቦል ቲቪ ብቻ ተዘጋጅተው ውድ ተመልካቾችን በመጠባበቅ ላይ ናቸው። አቦል ቲቪ በታህሳስ ወር አሁንም እንደተለመደው ውድ ተመልካቾች የሚጠብቋቸውን ጥራታቸውን የጠበቁ ድራማዎች ይዞ ቀርቧል።
ብርሀን
ብርሀን ድራማ የስነልቦና ጥያቄዎችን ለመመለስ የአንዲት የስነልቦና ባለሞያን ጉዞ ያስቃኘናል። ብርሀን ስኬታማ እና ቀና ባለሞያ ስትሆን፣ የታካሚዎቿን ጤንነት ለመጠበቅ መሰዋትነት ትከፍላለች። ነገር ግን በስራዋ ምክንያት የሚደርስባት ጭንቀት ለእራሷ ጤና የስነልቦና ባለሞያ እንድታማክር ትገደዳለች። ብርሀን ድራማ የአእምሮ ጤንነትን በቅርብ እየመረመረ የኢትዮጵያ ባህላዊ ህክምናን በማካተት ስለ አእምሮ ጤና ይበልጥ ያስተምረናል። ብርሀን ሰኞ ታህሳስ 28 ከምሽቱ 3:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይጀምራል።
ኤም ኤዲት
ኤም ኤዲት መጽሄት ወደ ፋሽን ሪያሊቲ ሾው ተቀይሮ ወደ አቦል እየመጣ ነው! ኤም ኤዲት በአዲስ አስተያየት የአፍሪካን ፋሽን እና አኗኗር የሚያቀርብ ሪያሊቲ ሾው ነው። ከኤም ኤዲት በአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት ውስጥ ያሉ ልዩ የአርቲስት እና አስገራሚ ስራ ፈጣሪዎችን ይዞልን ይቀርባል። ኤም ኤዲት ማክሰኞ ታህሳስ 29 ከምሽቱ 3:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ።
ተማሪ ቤት
ይህ ኮሜዲ ድራማ የተለያየ ባህል እና አኗኗር ያላቸው ስድስት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አብረው መኖር ሲጀምሩ የሚያጋጥማቸውን አስቂኝ እና አስተማሪ ገጠመኝ ያቀርባል። ተማሪ ቤት የማህበረሰባችንን ችግሮች እና የአኗኗር ጥያቄዎች የሚያነሳ አስተሳሰባችንን የሚመረምር ድራማ ነው። ተማሪ ቤት አርብ ታህሳስ 25 ከምሽቱ 9:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!
ድንቅነሽ
ድንቅነሽ ድራማ ተወዳጇ የአደይ እና የእንደአንድ ተዋናይት እታፈራሁ መብራቱን ይዞ የሚቀርብ አቅርቦት ነው። ከዚህ በፊት በአደይ እና እንደአንድ ያስደመመችንን እታፈራሁ መብራቱን በአዲሱ ድራማ ድንቅነሽ ለማየት በጉጉት እየተጠባበቅን ነው! ድንቅነሽ አርብ ጥር 9 ከምሽቱ 2፡00 ይጀምራል!
አቦል ቲቪ በታህሳስ እና ጥር ወር ምርጥ አቅርቦቶችን ይዞ ይቀርባል! ስለ ድራማዎቻችን ማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን በመጎብኘት ይከታተሉ!