በሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ በሚታየው ከፍተኛ የሆነ የስነ ምግባር ግድፈት የተነሳ ትምህርት ሚንስቴር ጠንካራ ህግ ያወጣል።
አዲስ የወጣው ሕግ የመጀመሪያ አላማ የትውልዱን የግብረ ገብ ክፍተት ለመሙላት በማሰብ የተራራቁ ሃሳቦች አቀራርቦ ለሀገር መቆም፣ ለትውልድ ትርፋማ መሆን፣ ለዘላቂ የተፈጥሮ ሰንሰለት እና ትውልድን በስነምግባር ለማነፅ ነው። የትምህርት ሚኒስቴር ለዚህ የትውልድ ማዳን ተግባር የሚመጥን እና የትውልድን ማነፅ ተግባር ግድ የሚለው ሀገር ወዳድ ሰው ማፈላለግ ጀምሮዋል። ለዚህ ሓሳብ ተግባራዊነት በልክ የተሰፉ ሰው በቀድሞው ዘመን የግብረገብ መምህር የነበሩ ኣሉ።
ከ1960ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ የግብረገብ መምህር የነበሩትና ለማህበረሰብና ለሀገር ብዙ ባለሙያ ሰዎችን ያፈሩት ስፍራሽ ብዙ በትምህርት ሚንስቴር ጥያቄ መሰረት ከጡረታ ተመልሰው መጥተዋል። የእሳቸው መምጣት ለዚህ ችግር መፍትሔ መሆኑ ታምኖበታል።
በሌላ በኩል በዋና ከተማዋ ከሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ የስነ ምግባር ግድፈት ከተገኘባቸው ሴት ተማሪዎች መካከል ስምንቱ ከከተማዋ ወጣ ብሎ በሚገኝ የቆየ አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ለሁለት ወራት በስፍራሽ ብዙና በባልደረቦቻቸው የስነምግባር ማሻሻያ ለመውሰድ ያለ ፍላጎታቸው ተገኝተዋል። ባህሪ የሚለመድ ነው በአንድ ጀንበር የሚመጣ የሱቅ እቃ ባለመሆኑ የተማሪዎቹ ጉዞ ከባድ ይሆናል ።
የባህሪ ለውጥ ሂደት ላይ የተመረጡትን ተማሪዎች ስም እና ማንነት ከስር ይመልከቱ።
ሳባ፦ አንባቢ እና ጥሩ ጭንቅላት አለኝ ብላ የምታስብ በመሆኗ አስታማሪዎቿንና ርእሰ መምህሩን በተደጋጋሚ ደደብ ብላ በመሳደብ የተከሰሰች ናት።
ህሊና፦ ብዙ ጊዜ በእጅ አመል የምትታማና እሷ ባለችበት አካባቢ ቁሳቁሶች እንደሚሰወሩ ሪፖርት የሚደረግባት ናት ።
ቅድስት፦ ብልጣብልጥ ራስ ወዳድና ጥቅሟን አስጠባቂ ተማሪ ነች። ተማሪዎችንና አስተማሪዎችን ለሁለት ከፍላ አባልታለች በሚል የተከሰሰች ተማሪም ነች።
ማርሲላስ፦ ቆንጆ፣ አማላይ ለመሆን የምትጥርና ነኝ ብላ የምታስብ ሞልቃቃ ባልተገባ አለባበስ ሜካፕና ሽቅርቅር ነገሮች የምትታወቅ ነች። ከሷ ከፍ ከሚል ጎረምሳ ጋር ከንፈር ለከንፈር ገጥማ እጅ ከፈንጅ ተይዛለች።
ሰላም፦ በሰው የምትመራና ታተዘዘችው ሁሉ የምታደርግ ብዙ ጊዜ ከተማሪዎች ጋር አብራ መስረቅ፣ መደባደብ፣ መጠጥ በመጠጣት፣ የትምህርት ቤት አጥር በመዝለል እና በሌሎችም ነገሮች ትከሰሳለች።
ረቂቅ፦ ሱሰኛ አጫሽ እና ሌላ በሚስጥር የተያዘ ጥፋት ያለባት። ሚስጥረኛ ቀልደኛና ተጫዋች። በመምህራኖቿ ላይ በማፌዝና በማላገጥ አለፍ ሲልም ቅፅል ስም በማውጣት የተከሰሰች።
ልዩ፦ ዝምተኛ ናት።
በስፍራሽ ብዙና በልጆቹ መካከል ያለውን የትውልድ ክፍተት አብረው ሁለት ወር ለመቆየት ያስችላቸዋል?
እነዚህ ተማሪዎች እርስ በእርስስ በአንድ ክፍል ውስጥ አብረው መዋልና ማደር ይችላሉ? ስፍራሽ ብዙስ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ እነዚህን ልጆች ማረም ይችላሉ?
ስፍራሽ ብዙ እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችንና ቁም ነገሮችን እያነሳና በቀልድ እያዋዛ እያዝናናም በ Episodical Deramatic Comedy ዘውግ በብዙ መንገድ ከተራራቁት ትውልዶች ጋር እየተጫወተ ለ አስራ ስድስት ክፍሎች ይነጉዳል።
#ስፍራሽ ብዙ ዘወትር ሐሙስ ምሽት 2:00 በ #አቦልቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይቀርባል!
በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed