ታኅሣሥ ወር ደርሷል እና ሁላችንም ከቤተሰብ ጋር ለማሳለፍ እና ምርጥ ምርጥ ድራማዎችን፣ ቴሌኖቬላዎችን ፣ ኮሜዲዎችን እና የአኗኗር ዘይቤዎችን በአቦል ቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ለመከታተል በጉጉት እንጠብቃለን። በእዚህ ወር የሚቀርቡት ድራማዎች እነዚህን ይመስላሉ፦
አፋፍ | ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2፡00
አፋፍ በ1984 ዓ.ም የዙማ መንደርን የመቀየር ህልም በታጠቁ የሁለት ጓደኛሞች ታሪክ ነው፡፡ ሁለቱ ወጣቶች ከእለታት በአንዱ ቀን ሰው ዝር በማይልበት ግዙፉ ተራራ ዙሪያ ሲሯሯጡ በድንገት አንድ በጣም ውድ ማዕድን ያገናኛሉ። የሰሞኑን ክፍሎች የአፋፍ ጥንዶችን ግንኙነት እና ፍቅር አድምቋል። እንቆጳ ለታምራት የፍቅር ጥያቄ ምን ትመልስ ይሆን?
ቁጭት | ከሰኞ - አርብ ከምሽቱ 2:30
ቁጭት ቴሌኖቬላ ታሪኩ የሚያጠነጥነው በህይወት ለመኖር ጥቂት ወራት ብቻ እንደሚቀረው ከተነገረው በኋላ የናፈቀውን ልጁን ዮናስን ለማግኘት ፍለጋ በጀመረ አባት ነው:: በባለፈው ሳምንት ክፍል ዮናስ አባቱ አቶ ፀጋዬ መሆኑን አውቋል። አቶ ፀጋዬን እንደ አባቱ የሚቀበል ይመስልዎታል?
ዳግማዊ | ሰኞ ከምሽቱ 3፡00
ዳግማዊ የተሰኘው ተወዳጅ ድራማ በጠበቃ ዳግማዊ እውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ ድራማ። በዛሬው ሳምንት ክፍል ታመነ እና ዳንኤል እንዴት እንደተዋወቁ አይተናል። ከዚህ በኋላ እንዴት ታመነ ወደ ግድያ ያመራ ይሆን?
አጋሮቹ | አርብ ከምሽቱ 1:30
በዚህ እውነተኛ ትዕይንት ላይ ጥንዶች የተለያዩ ውድድሮችን በማለፍ ወደር የሌለው የሰርግ ስነ ስርአት ለማሸነፍ ይወዳደራሉ። ጥንዶቹ ለሚያልሙት ውድድር ብለው ከባድ ውድድሮች ላይ መሳተፋቸውን ይቀጥላሉ። እርስዎ የትኞቹን ጥንዶች ነው የሚደግፉት?
በዚህ ወር አቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 የሚያዝናኛዎትን ያቀርብልዎታል። ትኩስ አቅርቦቶች እንዳያመልጥዎ አቦል ቲቪን ይከታተሉ!