abol tv logo

በመስከረም ወር እነዚህን የአቦል ቲቪ አቅርቦቶች ይመልከቱ

ዜና
12 ሴፕቴምበር 2023
አዲስ አመት አዲስ ታሪክ በአቦል ቲቪ።
new year new storyline september

በመስከረም በአቦል ቲቪ ሁሉም ትኩስ ነው። አዲሱን አመት ልክ እንደ ምግብ እና መጠጥ የሚያስደስት ልዩ ሀገረኛ መዝናኛ ይቀርባል። እርስዎ እነዚህን አቅርቦቶችን በመከታተል አዲስ አመትዎን ያድምቁ።

አፋፍ

ጣሪያ የነካ የገንዘብ ፍቅር ከማይመለስበት አፋፍ ላይ ደርሷል። እስከዳር ከእስር ቤት ተፈታለች እናም ወንጀሏን በፍርቱና ስም አላካዋለች። ነገር ግን ይህ ያልተዋጠላቸው ሰዎች አሉ እንቆጳ እና ዳግም እውነቱን የሚደርሱበት ይመስልዎታል?

ጊዜ

የተወሰደበትን ቤተሰብ እና እውነትን ለማስመለስ የሚታገለው አባት ትንቅንቅ ላይ ነው። በጀምበሩ የሚተማመኑ ሰዎች በቁጥር ጥቂት ቢሆኑ ንጽህናውን ለማስመስከር የሚያደርጉት ጥረት ትልቅ ምስጢሮችን እየነቀነቀ ነው። ሰናይትም የጌታቸው ባህሪ ጥርጣሬ አሳድሮባታል።

የቄሳር ዲናሮች

አሳ በማስገር ህይወቱን ለማቅናት የሚጣጣረው ይልቃል ያላሰበው ፈተና ተጋርጦበታል። ይልቃል በጀልባው ያሳፈራቸው ሰዎች ወንጀለኞች መሆናቸውን ሲደርስበት ፖሊሶች ምርመራቸውን ወደ ደቁ አዙረዋል። ከዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ይልቃል እንዴት ይወጣ ይሆን?

ፋኖስ

የሞትን ደጅ አንኳክቶ የተመለሰው አቶ አመሀ እራሱን ደብቆ ቤተሰቡን እና ወዳጆቹን መከታተሉን ቀጥሏል። አቶ አመሀ ከደረሰባቸው ምስጢሮች በየትኛው በጣም ተገርመዋል?

እንሞካከር

አርቲስቶቹ እና ታዋቂ ባለሞያዎቹ በእንሞካከር የምግብ ስራ ሞያቸውን እያስመሰከሩ እና አዝናኝ ፉክክርን እያሳዩ ነው።

እስካሁን ከቀረቡት ተወዳዳሪዎች ማንን ነበር የወደዱት?

እነዚህን አዝናኝ እና ልዩ አቅርቦቶች በአቦል ቲቪ መከታተል ይችላሉ። የትኛውን አቅርቦት በጉጉት እየተከታተሉ ነው?