Logo

የስቱዲዮ 30 አዲሱ ምዕራፍ አርቲስቶችን እንተዋወቅ - ስቱዲዮ 30

ዜና
03 ሴፕቴምበር 2021
በምዕራፍ 2 የሚቀርቡት አርቲስቶች ማን ናቸው?

ስቱዲዮ 30 አንድ ቤት ውስጥ አብረው ለ30 ቀን እየኖሩ በቀረበላቸው የሙዚቃ መሳሪያ አልበም የሚያዘጋጁ አርቲስቶችን የሚያቀርብ ሪያሊቲ ቲቪ ነው። በምዕራፍ 2 ውስጥ የሚቀርቡት አርቲስቶች ማን እንደሆኑ እንተዋወቅ።

1. ሄለን - ዘፋኝ

ሄለን ሙዚቃ ከልጅነቷ ጀምሮ ትወድ ነበር ግን ከቤተሰቧ ተቀባይነት አልነበረውም። የሙዚቃ ስራ ፍቅሯን እና ፍላጎቷን በማየታቸው ፍቃዳቸውን ሰጥተዋታል። ሄለን ከሙዚቃ በስተቀር ሞዴሊንግ እና ማስታወቂያ ላይ ትሰራለች በተጨማሪም  በቅርብ የሚለቀቅ አልበም አላት። የምትወዳቸው ዘፋኞች እነ ዘሪቱ፣ ቤቲ ጂ እና ጂጂ ናቸው እና ወደፊት በሙዚቃ፣ ሞዴሊንግ እና ፊልም ስራ መቀጠል ትፈልጋለች።

2. ዚዲክ - ዘፋኝ

ከልጅነቷ ጀምሮ ሙዚቃ ትወድ ነበር እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለችበት ጊዜ እናቷ ብቻዋን ስላሳደገቻት ተማሪዎች በሚየጠቋት ጊዜ ላይ በጣም የሚያጽናናት ሙዚቃ ነበር። ዚዲክ የራሷ ልዩ የሆነ ስራ ማውጣት ትፈልጋለች እናም መድረክ ላይ የማቅረብ ልምድ አላት። ወደፊት ዚዲክ በስራዋ እናትዋን የምታኮራ እና ለሴቶች እና እናቶች ጠበቃ የምትሆን አርቲስት እንድትሆን ትፈልጋለች።

3. አማኑኤል - ዘፋኝ

መዝፈን የጀመረው ከዘጠኝ አመቱ ነበር እና የዘፈን ፍቅሩ በእናቱና እህቱ ተደግፎ ነው ያደገው፣ እናቱን ለማኩራት ይመኛል። ከሚወደው አርቲሲት ጀስቲን ቢበር ጋር አንድ ቀን ሙዚቃ ለመስራት ይፈልጋል። ባላገሩ እና መረዋ የተባሉ ውድድሮች ላይ ተሳትፎ ነበር፣ መረዋ ውድድር በተቋረጠበት ጊዜ ላይ ከሶስት አብረው የተወዳደሩ ጓደኞቹ ጋር የሙዚቃ ባንድ ጀምሮ ሰርቶ ነበር። አማኑኤል በስቱዲዮ 30 ላይ ለየት ያለ ሙዚቃ መስራት ይፈልጋል።

4. አይዛክ - ፕሮድዩሰር

ፕሮድዩስ ማድረግ የጀመረው በኤሌክትሮኒክ አይነት ሙዚቃ ነበር:: አሁን ግን የተለያዩ አይነት ሙዚቃዎችን ፕሮድዩስ ማድረግ ይችላል። ለየት ያለ ስሜት የሚገልጹ አዳዲስ ሙዚቃዎችን ያደንቃል እናም በስራው ለየት ያለ ሙዚቃ ማቅረብ ያቅዳል። አስተዳደጉ አሁን ለአለው ባሕሪ ዋናው ምክንያት ነው። ቤተሰቡን እጅግ ያከብራል።

5. ነብዩ - ዘፋኝ

ኳስ መጫወት እራሱን የሚገልጽበት መንገድ ከመሆኑ የተነሳ ከልጅነቱ ጀምሮ ኳስ ተጫዋች መሆን ይፈልግ ነበር። በተለያዩ ችግሮች ምክነያት የኳስ መጫወት ህልሙ ስላልተሳካ ወደ ሙዚቃ ማተኮር ጀምሯል። ይሆ ህይወት ከቤተሰቡ እስተዳደግ ጋር የተጋጨ ስለነበር ፈተና ሆኖበት ነበር። ነብዩ የሰውን አኗኗር መቀየር እና ከሰው ጋር በሙዚቃ መግባባት ይፈልጋል። ዛሜር አኩስቲክ ባንድ ውስጥ ዘፋኝ ነው እናም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ነጠላ ዜማ ይለቃሉ። የሚወዳቸው አርቲስቶች እዮብ መኮንን፣ ሀይሉ አመርጋ፣ ግርማ በየነ እና ቸሊና ናቸው። ስቱዲዮ 30 ለአርቲስቶች ሙዚቃ እንዲሰሩ የሰጣቸውን እድል በጣም አሪፍ ነው ብሎ ያስባል።

6. ቢኒያም (ቀጭን ጠጅ) - ፕሮድዩሰር

ሙዚቃ መስራት ከጀመረ ስድስት አመት ሆኖታል። ሶስት አልበም፣ አራት ነጥል ፕሮጀክቶች እና አንድ ጠብታ የተባለ ኢፒ ላይ ሰርቷል።ብልዝ የተባለ የሙዚቃ ዘውግ ከባልደረባው 251 ጋር ፈጥረዋል፣ ዘውጉን የፈጠሩት እነሱ መስማት የሚወዱትን አይነት ዘውግ ሰው እንዲዝናናበት ፈጥረዋል። ስቱዲዮ 30 ላይ በሚሰራው አልበም ላይ መሳተፍ በመቻሉ በጣም ደስተኛ ነው።

7. ሊና - ዘፋኝ

ሙዚቃ ከልጅነቷ ጀምሮ ትወድ ነበር። አሁን የምትታወቀው በቲክ ቶክ ላይ በምታቀርባቸው ቪዲዮዎች ነው። የምትወደው አይነት ዘፈን ነው እና የምትወዳቸው አርቲስቶች እነ ጄምስ ብራውን እና ክርስቲና አጉሌራ ናቸው። የሚያነሷሷት ነገሮች ፊልም እና ኮሪያን ድራማዎች ናቸው። ሊና ወደፊት የራሷ የተባለ ስራ መልቀቅ እና ሙዚቃ መማር ያልቻሉ ሰዎችን መርዳት ነው።

እነዚህ ሰባት አርቲስቶችን ለሚቀጥለው 30 ቀናት እንከታተላለን። እስካሁን ማንን እንደወደዱ ያሳውቁን!

ስቱዲዮ 30 ሐሙስ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!