abol tv logo

ስቱዲዮ 30፣ የአቦል አጓጊው የሙዚቃ ሪያሊቲ ቲቪ ሾው!

ዜና
13 ኤፕሪል 2021
ስለኢቶጵያውያን ሙዚቃ የተሰራ ሪያሊቲ ቲቪ ማየት ፈልግው ያውቃሉ? በአቦል ቲቪ ላይ ይሄንን ስቱዲዮ 30 የሚባል ትርኢት ማግኘት ይችላሉ!

ስለ ስቱዲዮ 30

ይህ ሪያሊቲ ቲቪ የሚከተለው አንድ ቤት ውስጥ አብረው ለ30 ቀን እየኖሩ በቀረበላቸው የሙዚቃ መሳሪያ አልበም የሚያዘጋጁ አርቲስቶችን ነው።

ስቱዲዮ 30ን ለማየት ሶስት ምክነያቶች

የኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ

የኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ብዙ እንደሆነ እናቃለን ነገር ግን የዚህ ጊዜ አርቲስቶችስ? በምን ይመስልዎታል የድሮ ሙዚቃ ካሁን የሙዚቃ ስራ ጋር የሚመሳሰለው? የዚህ ዘመን አርቲስቶች የድሮ የሙዚቃ አሰራርን እየተከተሉ ነው ወይስ የራሳቸውን አዳዲስ ሃሳብ እያካተቱበት ነው? ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ በስቱዲዮ 30 ላይ ያግኙ!

የአርቲስቶች ፈጠራ ሂደት

ስቱዲዮ 30ን በመከተል አርቲስቶች ፈጠራ ሂደታቸው ምን እንደሚመስል እና የአልበም ፕሮዳክሽን ስራ እያንዳንዱን ደርጃ ማወቅ ይችላሉ። ከአርቲስቶቹም ጋር ባለን የጥያቄ እና መልስ ጊዜ የሙዚቃ ፈጠራ ሂደታቸውን ማወቅ እንችላለን።

የፕሮድዩሰር አሰራር ሂደት

በጣም ያስደነቀዎት ሙዚቃ ሰምተው ያቃሉ? ያንን አስደናቂ ሙዚቃ ከአርቲስት ጋር በጋራ ሰርቶ ያቀረበው ፕሮድዩሰር ማን ነው ብለው አስበው ያቃሉ? ስቱዲዮ 30 ላይ አርቲስት እና ፕሮድዩሰር እንዴት ተባብረው የሚያዝናና ሙዚቃ እንደሚያዘጋጁ ማየት ይችላሉ!

ስቱዲዮ 30 በአቦል ቲቪ ቻናል 146 ዕሮብ ከምሽቱ 2:30 እና ቅዳሜ ከምሽቱ 3፡00 ይተላለፋል!