Logo
Nafikot S2

በናፍቆት ድራማ የመጨረሻ ክፍል የምንጠብቃቸው 3 ነገሮች። - ናፍቆት

ዜና
14 ዲሴምበር 2021
በጉጉት እየጠበቅናቸው ያለነው መልሶች።

የናፍቆት ድራማ ምዕራፍ 2 ላይ ብዙ ልብ አንጠልጣይ ጊዜያቶችን አቅርቧል። እነዚህ ጊዜያት ያመነጩትን ትልልቅ ጥያቄዎች እነዚህ ናቸው።

  1. የስመኘው ምርጫ

ቃል አብ በተደጋጋሚ ሲያይ የነበረው ህልም ስመኘው እንደሚክደው ነበር። ይህ ቢሆንም ግን የረጅም ጊዜ ጓደኛውኝ ተማምኖ ህልሙ ያሳደረበትን ጥርጣሬ ለመርሳት ሞክሯል። በትክክል መርጧል ብለው ያስባሉ? ሲያፈላልጉት የነበረው የባዳድ ገዳይ ናርዶስ መሆኗ ተጋልጧል ግን ናርዶስ ማርገዟን አሳውቀዋለች። ስመኘው ማንን ይመርጥ ይሆን?

  1. ገላ እና ልጆቿ

የገላ በሽታ እየባሰ በመሆኑ ልጆቿ ከእናታቸው የሚለዩበት ቀን እየተቃረበ መሆኑን መቀበል ኖሮባቸዋል። ከቤታቸው በሰናይት ምቀኝነት ምክነያት ሲባረሩ ለገላ ይስዘጋጁትን አልበም አጥተዋል። ገላን ሳያጡ አልበሙን ደግመው ማዘጋጀት ይችሉ ይሆን?

  1. የግሩም ዝግጅት

ግሩም እና ቃልአብ ለፀሀይ ባላቸው ፍቅር ምክነያት ወንድማማችነታችውን እረስተው ውድድር ውስጥ ገብተዋል። በመሀላቸው ያለው ውድድር በአካባቢያቸው ያሉትን ሰዎች እና እራሳቸውን አደጋውስጥ ከቷችዋል። ባለፈው የናፍቆት ክፍል ላይ ግሩም እራሱን ለግጥሚያ እያዘጋጀ ነበር፣ ከቃልአብ ጋር ለመጭረሻ ጊዜ ሊጋጠሙ ይሆን?

የምዕራፍ 2 የመጨረሻ ክፍል በጉጉት እየተጠባበቁ ነው? አስተያየትዎን ያሳውቁን!

 

ናፍቆት ማክሰኞ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ዲኤቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!