Logo
Nafikot Slim Billboard Desktop 1600x160

ድብቅ ጥፋት - ናፍቆት

ዜና
03 ኦገስት 2021
ህሊናን የረበሹ ድብቅ ጥፋቶች።

ዮሀንስ ስለወንድሙ ንፅህና ገላን ለማሳመን ሙከራውን ቀጥሏል። የአዳነህ ከእስር ቤት መለቀቅ ለጥንዶቹ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል ብሎ በማመኑ፣ ስለ ስላደረገው ነገር እውነታውን  ለገላ መንገር ይፈልጋል።

ሰናይት ከገላ ቤተሰብ ጋር ለመኖር በመምጣቷ ቤተሰቡን ቢረብሽም ግን ገላ በፀፀቷ ምክነያት ሁሉን ችላ ለመኖር ዝግጁ ነች።

ገላ  ባሏ እህቷ ላይ ባደረሰባት ጉዳት የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማታል።  ሰናይት ላይ የደረሰው ጉዳት በዮሀንስ ምክነያት መሆኑን ብትረዳ ይቅር ትለው ይሆን? ወይስ እስካሁን እውነቱን በመደበቁ የበለጠ እንደተካደች ይሰማታል?

በገላ ቤተሰብ ውስጥ በሁለቱ ልጆቿ መጥፋት ምክኒያት ከፍተኛ ልዩነቶች ተፈጥረዋል። ። ግሩም እስርቤት በቆየበት ወቅት እውነተኛ ማንነቱ ፈጦ ወጥቷል። ወንድሙን ለመግደል ሙከራ እስከማድረግ ከደረሰ በኋላ ወደ ፀሀይ ለመመለስ ይችል ይሆን?

የነዚህን ጥያቄዎች መልስ ለማየት ናፍቆት ድራማን ይከታተሉ!

ናፍቆት ማክሰኞ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይቀርባል!