Logo
Abol Duka Zuret S1 Slim Billboard Desktop

የዙረት እና ናፍቆት ጅማሪ የአቦል ቲቪ ታዳሚዋችን ልብ አንጠልጥሏል

ዜና
04 ጁን 2021
የአቦል ቲቪ ውድ ተመልካቾች ስለ አዲስ ድራማ አቅርቦቶቹ ምን ብለዋል?

በዚህ ሳምንት ሁለት አዳዲስ ድራማዎች በአቦል ቲቪ በመጀመራቸው፣ ተመልካቾች ልዩ የድራማ ምርጫዎች ቀርቦላቸው ነበር!

ማራኪው ዙረት ድራማ እንደነ ዳንኤል ተገኝ ፣ ሳምሶን ታደሰ እና ሩታ መንግስተአብ ያሉ ታዋቂ ተዋንያንን ወደ አቦል ቲቪ ይዞ ቀርቧል። ይህ ትዕይንት የሚከተለው ከሃገሪትዋ በህግወጥ መንገድ ብዙ ብር ለማውጣት የሚያቅደውን የወንጀል ድርጅት መሪ ለመያዝ የሚጥረውን ኪዳን የተባለ የፖሊስ ሰላይን ነው። እራሱን ሹፌር አስመስሎ ድርጅቱ ውስጥ በመገባቱ ኪዳን የልጅነት ፍቅኛው የድርጅቱ መሪ እጮኛ መሆንዋን ይረዳል፣ ተልእኮውም ይወሳስባል።

በመጀመሪያው ክፍል ላይ ያታየው የኪዳን እና የምዕራፍ ግንኙነት ልባችንን አንጠልጥሏል።

ሌላ በዚህ ሳምንት የተጀመረው ድራማ ናፊኮት ነው ፡፡ የመጀመሪያው ክፍል ስቤተሰብ እና የተከለከለ ፍቅር በሆነው ታሪክ መስመሩ የታዳሚዎቻችንን ልብ ነክቷል፡፡


ናፍቆት ስለ አንዲት ጎበዝ ዘፋኝ እና በልጅነቷ ወልዳ ካላአባት ስላሳደገችው ልጇ ቃላብ ነው። ቃላብ ከእናቱ ገላ ጋር ምንም ሳያጣ ያድጋል፣ የዘፈን ፍቅሯንም ይጋራል ግን እህት እና ወንድም በመፈለጉ ይጨቀጭቃታል። ስለዚህም ገላ ለቃላብ ብላ ሙዚቃ ፍቅር ያላቸው አራት ልጆች ከጉዲፈቻ ወስዳ አብራ ታሳድጋቸዋለች። እህቱን በማፍቀሩ ቃላብ ከእናቱ እና ወንድሙ ጋር ሲጣላ ከቤት ይጠፋል።

በአዝናኚ ትዕይንቶች የተሞላ ሳምንት ነበር። ድራማዎቹን ተከታትለዋል? በዙረት እና ናፍቆት ምን እንዳዝናናዎ አስተያየትዎን ያሳውቁን!

ዙረትን ሰኞ ከምሽቱ 02:30 እና ናፍቆትን ማክሰኞ ከምሽቱ 02:30 ይከታተሉ!