Logo
Nafikot Slim Billboard Desktop 1600x160

የቤተሰብ ፍቅር - ናፍቆት

ዜና
17 ኦገስት 2021
ቤተሰቡን ጸብ ያለያያቸዋል።

በፀሀይ እና ግሩም ፍቅር ማሀል ለመግባት የሞከረ ሰው የግሩም ጠላት ሆንዋል። ግሩም ከቃልአብ አልፎ የግድያ ሙከራውን አንዋር ላይ ቀጥሏል፣ ፀሀይ ይህን በማወቋ ቤተሰቧን ለመጠበቅ ምን አይነት ውሳኔ ላይ ትደርስ ይሆን?

ፖሊስ መኮንን ሰውነት ኮማንደሩን መተካቱ አልተዋጠለትም፣ የኮማንደሩን ምክንያት ሳያረጋግጥ ስራውን መቀበል አይፈልግም። ሰውነት እንዴት የሚደርስበት ይመስለዎታል? ወ/ሮ ሽታዬ እና እዮብ በወንጀሉ ውስጥ ምን ጨምረዋል?

ገላ እና ስናፍቅ ሆስፒታል በሚያሳልፉት ጊዜ ስለቤተሰባቸው በመጫወት ይጽናናሉ። ምን ያክል ጊዜ እንዳላቸው ባለማወቅ የሚሰማቸውን ፍራቻ ለመርሳት ይሞክራሉ።

የእናታቸው በሽታ እያስጨነቃቸው ባለ ጊዜ የግሩም ጥቃት ልጆቿን ይጎዳቸዋል፣ ግሩም ከጸሀይ ጋር ሊያለያዩት ይሞክራሉ ብሎ የሚያስባቸውን ሰዎች ለማስወገድ ያቅዳል።

ቃልአብ ወደቤት ይመለሳል እናም ከጓደኞቹ ጋር ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ይዘጋጃል፣ ስለገላ መታመም ይነገረው?

ናፍቆት ምዕራፍ 1 ተጠናቋል፣ ምዕራፍ 2 ን በጉጉት ይጠብቁ!