በዚህ ሳምንት ምን ተፈጥርዋል?
ወ/ሮ ሮማን ለሌሎች፣ በተለይም ለአዴይ፣ ያላቸው ባህሪ ለውጥ እያመጣ ቢመስልም በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ማሴር አላቆሙም ፡፡ ማኪ በመጨረሻ የእናቷን ኩባንያ ለመቀማት ፊርማ አገኘች ግን የክህደት ዋንጫ ቢኖር አቶ ግርማ ያሸንፉት ነበር፡፡ አቶ ግርማ ው/ሮ ሮማንን ችል ያልዋችው ውሽማቸውን በማስረገዝ ብቻ ሳይሆን ከእነሱ ጋር ቤታቸው አብራ እንድትኖ በማምጣት ነው፡፡
ወ/ሮ ሮማን ምን የሚያደርጉ ይመስላችዋል?
ከዚህ ሊመለሱ ይችላሉ ብለው ያስባሉ? አቶ ግርማ ውሽማቸውን ደጋግመው ወደ ቤታቸው በማምጣት ንቀቷን እንድትቀጥል ፈቅደዋል፡፡ ወ/ሮ ሮማን በባለቤታቸው ክህደት ምክነያት ወደ መጠጥ ሲዞሩ እና ሁሉንም ሰው ርቀው ሲኖሩ ተመልክተናል ነገር ግን የዚህ ሃዘን መንስኤን ለማስወገድ ሲወስኑ ገና አላየንም። የዚህ ጋብቻ ፍጻሜ የመጨረሻ ግፊያ ይሄ ይሆናልን? ምን ያደርጋሉ?
የተፈጠረውን ረስተው አስካሁን አንደኖሩት ይቀጥላሉ፤
ለልጆቻቸው እና ስራቸው ሲሉ ሁሉንም ችለው መኖር ይቀጥላሉ? እስካሁን ርቀው ቢኖሩም፣ ወ/ሮ ሮማን ለልጆቻቸው እና ለኩባኒያቸው ያላቸው ፍቅርን አይተናል ስለዚህ ለዚህ ሲሉ ምንም ነገር አለማድረግ ሊወስኑ ይችላሉ ፡፡ ለባለቤታቸው ምንም ፍቅር እንደሌላቸው ግልፅ አድርገዋል ነገር ግን በጨዋታ ላይ ያሉ ሌሎች ምክንያቶች ሁል ባሉበት ሊያቆዩዋቸው ይችላሉ ፡፡
ምንም ሳይሉ ይቀጥላሉ፤
የሆነ ጊዜ ውስጥ አንዳንድ ሰዎች እንደታሰሩ እና ምንም ነገር ማድረግ እንደማይችሉ ስለሚሰማቸው ሁሉም ነገር ምንም መምሰም ያቆማል፡፡ ወይዘሮ ሮማን ለባላቸው ውሽማ ያላቸውን ጥላቻ ከዚህም በፊት አሳውቀዋል፣ ግን የአቶ ግርማ ብቸኛ ምላሽ እስካሁን ሁሉም በሚስታቸው ሃሳቡ እንደሆነ እና ውሸት እንደሆነ ነው፡፡ ይህ ማንኛውም ሰው ወደ መጠጥ ወይ እብድነት እንዲዞር ሊያደርግ የሚችል ግፊት ነው፡፡ እርሳቸው ወ/ሮ ሮማን ትክክል እንደነበሩ ሁሉም ማስረጃዎች ቢኖሩም እስካሁን ምንም አለማድረጋቸው አይገርምም፡፡
በፌስቡክ እና ትዊተተር ላይ ው/ሮ ሮማን ምን ይሚያደርጉ እንደሚመስላቹ እና ምን ቢያደርጉ ይሻላል ብላቹ እንደምታስቡ ያሳውቁን!
የዚህ ሳምንትን የአደይ ክፍሎች ካመለጥዎ ይሄን አድማቂ ቪዲዮ ይመልከቱ፤
አደይን ከሰኞ እስከ አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ ቻናል 146 ላይ አያምልጦ።