ተወዳጁ የዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ ቻናል አቦል ቲቪ ልዩ ልዩ ትዕይንቶችን ይዞ ቀርቧል። እነዚህ አስደናቂ ድራማዎች ምዕራፍ 2 በአቦል ቲቪ የሚጀምሩበትን ቀናት ለማወቅ ከዚህ በታች ይመልከቱ!
አስኳላ ምዕራፍ 2::
በምዕራፍ 1 ላይ የኔታ አስኳላ ትምህርት ቤት ከልጆች ጋር ሲማሩ ቆይተዋል፣ አሁን ግን ባለቤታቸው እምወድሽ ከየኔታ ጋር አብረው አስኳላ ትምህርት ቤት መማር ይፈልጋሉ። በምዕራፍ 2 ውስጥ ጥንዶቹ አስኳላ ትምህርት ቤት አብረው መማር ይጀምሩ ይሆን? ወይስ የኔታ በላቸው ምዝገባውን እንዳይቀጥል ያሳምኑታል?
የኔታ እና የአስኳላ አስተማሪዎች በምዕራፍ 2 ይዘው የሚቀርቧቸውን አስቂኝ ጊዜያት እንዳያመልጥዎ መስከራም 5 ከምሽቱ 1:30 ይከታተሉት!
ስቱዲዮ 30 ምዕራፍ 2::
ስቱዲዮ 30 ለሙዚቃ ወዳጆች የተዘጋጀ በአርቲስቶች መካከል የሚካሄድ የአልበም አሠራር ውድድር ነው። ምዕራፍ 1 ላይ የቀረቡት አርቲስቶች አስደናቂ አልበም አቀናጅተው ነበር። መጪው ምዕራፍ አዳዲስ አርቲስቶችን ነሐሴ 27 ከምሽቱ 2:30 ይዞሎዎት ይቀርባል!
ናፍቆት ምዕራፍ 2::
ናፍቆት ምዕራፍ 1 ልባችንን አንጠልጥሎ ነበር የተጠናቀቀው። ግሩም ለአንዋር ባለው ጥላቻ ምክንያት ሊገለው ሲሞክር ፀሀይ አይታለች። ፀሀይ ይሄንን በማየቷ ስለቤተሰቧ ደህንነት እየተጨነቀች ነው። ቃልአብ እና ስመኘው የሚኖሩበትን ለቀዋል፣ ይሄ ውሳኔ ቃልአብ ፀሀይን ረስቶ አዲስ ህይወት ሊጀምር ይፈልጋል ማለት ይሆን?
የገላ ጤና እየተሻሻለ ባለመሆኑ ቃልአብን ለማግኘት ከአንዋር ሀሳብ ጋር ትስማማ ይሆን? የገላ ቤተሰብ እንዴት እንደሚሆን ለማወቅ ናፍቆት ምዕራፍ 2 መስከረም 11 ከምሽቱ 2:30 ይከታተሉት!
ባሻ ይሁን ኮሜዲ::
ባሻ ይሁን አዲስ ኮሜዲ በአቦል ቲቪ ነሐሴ 25 ቀን ይቀርባል። ይህ ኮሜዲ ባሻ የተባለ ችግር የማያጣው ሰው እና ከልጆቹ፣ የቤት ሰራተኞቹ እና ጎረቤቶቹ ጋር ያለውን የተለያየ ግንኙነት ይሳያል። ይህ አስቂኝ ድራማ በአቦል ቲቪ ነሐሴ 25 ከምሽቱ 1:30 ይጀምራል!
እነዚህን ልዩ ልዩ ልብ አንጠልጣይ ትዕይንቶችን ለመመልከት በጉጉት እየጠበቁ ነው? የትኛውን የአቦል ቲቪ ድራማ እየተጠባበቁ እንደሆነ ያሳውቁን!