Logo

ስለ በእምት ሙሉጌታ በፌስቡክ ላይቭ የሰማናቸው አምስት ነገሮች

ዜና
22 ጁን 2021
የአደይ ተዋንያን በእምነት ሙሉጌታ ልክ እንደገጸባህሪዋ አስደሳች ነች፡፡

በተወዳጁ የአቦል ቲቪ ድራማ ላይ አደይን ሆና የምትተውነው በእምነት ሙሉጌታ ባለፈው አርብ ምሽት ከድራማው አድናቂዎች ጋር በፌስቡክ ላይቭ ቻት ቆይታ አድርጋለች፡፡ በአቦል ቲቪ የቀረቡትን ጥያቄዎች በመመለስ እና ስለ ህይወቷ እና ስራዋ በማጫወት ከተመልካቾች ጋር ጥሩ ጊዜ አሳልፋለች። የአደይ ድራማ ፌስቡክ ላይቭ፣ ወ/ሮ ሮማንን ሆና ከምትተውነው ሰርካለም ጌታሁን ጋር አርብ ከምሽቱ 1:30 በአቦል ቲቪ ይቀጥላል።

ስለ በእምነት የሰማናቸው ነገሮች እነዚህ ናቸው፡

  1. በእምነት ለመጀመሪያ ጊዜ የተወነችው በአደይ ድራማ ላይ ነው

ፌስቡክ ላይቭ ቻት ላይ በእምነት ተዋናይ የመሆን የልጀነት ህልሟ እንደነበረ ነግራናለች። ቢሆንም አደይ ላይ ስትተውን የመጀመሪያ ጊዜዋ እንደሆነ አሳውቃናለች። የአደይ ተመልካቾች የበእምነት ትወናን ምን ያክል እንደሚወዱት እና የአደይን ገጸ ባህሪ ያቀረበችበት መንገድ በጣም እንደሚያስደስት ገልጸውላታል፣ ወደፊትም በሌሎች ፊልሞች ለመመልከት ያላቸውን ጉጉት ገልጸዋል፡፡

  1. የምትወዳቸው አርቲስቶች

አጋፋሪ የተባለው የአቦል ቲቪ ድራማ ላይ እየተወነ የሚገኝው አለማየው ታደሰ እናም ከሴቶች አርቲስት ደግሞ ሙሏለም ታደሰን እና ሀረገወይን አሰፋን እንደምታደንቃቸው ነግራናለች።

  1. ትወና እና ትምህርት

በእምነት በዚህ ጊዜ ትወና ላይ ሙሉ ትኩረቷን ሰታለች ግን ተማሪ እንደሆነችም አሳውቃናለች።

  1. ዲዛይን መማር ትፈልጋለች

በእምነት በትዕይንቱ ተጽዕኖ ምክንያት የዲዛይን ትምህርት ቤት ለመሄድ እያሰበች መሆኑን ገልፃለች። አደይ ለዲዛይን ያላትን ፍቅር በድራማ ውስጥ አይተናል ይሄ የዲዛይን ፍቅር የኛን ብቻ ትኩረት እንዳልሳበ አይተናል።

  1. አደይን እና በእምነትን የሚያመሳስላቸው ነገር

ተግባቢነቷ ከአደይ ጋር ያመሳስላታል ብላ እንደምታምን አሳውቃናለች።

በዚህ ሳምንት አርብ ከምሽቱ 1:30 ደግሞ ወ/ሮ ሮማንን ሆና የምትተውነው ሰርካለም ጌታሁን ጋር በፌስቡክ ላይቭ ቻት ትቀርባለች። ጥያቄዎን ለማቅረብ ላይቩን በአቦል ቲቪ ፌስቡክ ይከታተሉት!

አደይ ምዕራፍ 2 ወደ አቦል ቲቪ ሊመለስ አንድ ሳምንት ብቻ ቀርቶታል! ከሰኞ እስከ አርብ ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 እንዳያመልጥዎ።