Logo
Abol Duka Zuret S1 Slim Billboard Desktop
channel logo

Zuret

466DramaPG13

የምዕራፍ ፈተና – ዙረት

ዜና
02 ዲሴምበር 2021
ምዕራፍ እነዚህ ከባባድ ችግሮችን ስትታገል ቆይታለች።

ምዕራፍ ወደ ኢትዮጲያ የመጣችው ሰርግዋን ለማቀድና ቤተሰቧን ለማግኘት ነበር። ነገር ግን የቀደመ ህይወቷን ማስታወስ አለመቻልዋና እጮኛዋ የተደበቀ ህይወት ያለው ጨካኝ ወንጀለኛ መሆኑ የተለያዩ እንቅፋቶች ላይ እንድትወድቅ አድርገዋታል፡፡ ምዕራፍ ኢትዮጲያ ከመጣች ጀምሮ ያጋጠሟት ሶስት ትልቅ ፈተናዎች እነዚህ ናቸው።

  1. የኪዳን ማንነትን ማስታወስ

ምዕራፍ አሁን የማታስታውሰው የልጅነት ፍቅሯ ኪዳን፤ ሹፌር መስሎ ለእጮኛዋ እንደሚሰራ አላወቀችም፡፡ ምክንያቱም ከሀገር ውጪ የደረሰባት አደጋ የቀደመው ህይወቷን እንድትረሳ አድርጓታል፡፡ ነገር ግን አሁን ኪዳንን ስትተዋወቀው የተረሳ ስሜቷ እና ትዝታዋ ተጭሮባታል ።  ግን የትኛዋ ለሰርጓ የምትዘጋጅ ሙሽሪት የልጅነት ፍቅሯን ማስታወስ ትፈልጋለች?

1638436258 56 screenshot 2021 12 02 at 11.00.11

  1. የሱራፌል እውነተኛ ማንነት

ሰው ፍቅር ይዞት ከፍቅረኛውጋ አዲስ ህይወት አብሮ ለመገንባት ሲዘጋጅ ስለእጮኛው ዋና ዋና መረጃዎችን አውቃለው ብሎ መተማመን አለበት። ከምዕራፍ የተደበቁት የሱራፌል ምስጢሮች ግን ከምታውቀው እጮኛዋ ፍጹም የራቁ ብቻ ሳይሆኑ፣ ህይወቷንም በተደጋጋሚ አደጋ ላይ የጣሉ ናቸው። ከዚህም አልፎ ሱራፌል የራሱን ፍላጎት ለማሳካት ሲል የእስዋን ደህንነት አደጋ ላይ ከመጣል ወደኋላ የማይል ሰው ነው።

1638436394 32 screenshot 2021 12 02 at 10.56.36

  1. የሰብለ ክህደት

ከሀገር ውጪ ብቸኛ ሆኖ የኖረ ማንኛውም ሰው አብሮ አደግ ጓደኛውን ሲያገኝ ያለምንም ጥርጣሬ በደስታ ይቀበለዋል። ስለዚህ ምዕራፍ ሰብለን በደስታ ተቀብላት ስለህይወቷ ስታጫውታትና እጮኛዋን ስታስተዋውቃት ከእስዋ የጠበቀችው ጓደኝነት እንጂ በምቀኝነትና በቅናት የተነሳሳ ክህደትን አልነበረም። ሰብለ ግን ሱራፌልን ካገኘችው ጀምሮ የምዕራፍ የሆነውን ሁሉ የራሷ ለማድረግ ተነስታለች።

1638436526 32 screenshot 2021 12 02 at 10.58.28

የቀደመው ህይወቷን መርሳት፣ የእጮኛዋ የተደበቀ ማንነትና የልጅነት ፍቅሯን ማጣት። የምዕራፍ ፈተናና ሀዘን ማለቂያ አጥቶዋል፣ በሚቀጥሉት የዙረት ድራማ ክፍሎች ደግሞ ምን ይጠብቃት ይሆን?

ዙረት፡፡ ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ይከታተሉ!