channel logo
Yerekik menged S1

የረቂቅ መንገድ ገጸ ባህሪዎችን መጨረሻ እንገምት

ዜና
27 ሴፕቴምበር 2024
ግምትዎን በመምረጥ ያሳውቁን!
yerekik menged finale article

የረቂቅ መንገድ ድራማ ረቂቅ ፍትህ ለማግኘት ብላ የጀመረችው ጉዞ ምን ያህል የእሷን እና በአካባቢዋ ያሉትን ሰዎች ህይወት እንደቀየረው አሳይቶናል። በአሁን ሰዓት ረቂቅ፣ የእናት እና ልጅን ህይወት አትርፋ፣ የባቷን ድርጅት በቁጥጥሯ አስገብታ እና ፍትህ ለማግኘት የምትወዳቸውን ሰዎች ለመሸወድ ተገዳለች። ህይወታቸው በረቂቅ ምክንያት የተቀየሩት ሰዎች እነዚህ ናቸው፣ መጨረሻቸውን መገመት ትችላላችሁ?

ኒና ገዛህኝ

ኒና ከልጅነቷ ጀምሮ የነበራት ፍላጎት የአባቷን ድርጅት መምራት እና በአባቷ ከወንድሞቿ እኩል መታየት ነበር። ይሄን ለማሳካት ኒና ብዙ እርምጃዎችን ወስዳለች፣ በሰዎች ህይወት ውስጥም ጣልቃ ገብታለች ግን እንደዚህ ስታደርግ መብት አለኝ ብላ ስላመነች ነበር። ነገር ግን አሁን አስቴር ኒና የአቶ ገዛህኝ ልጅ አለመሆኗን አጋልጣለች፣ ይህ ማለት ኒና በጥንቃቄ የገነባችው ማንነት ትክክል አይደለም ማለት ነው።

Yerekik menged S1
yerekik menged poll 6

የኒና መጨረሻ ምን ይመስላችኋል?

Click here to make your selection
እራሷን ታሻሽላለች
እናቷ ስለዋሸቻት ትቀጣታለች

መሳይ ገዛህኝ

ወደ ቤተሰቡ ረቂቅ ስትመጣ መሳይ ማንነቱን የማያውቅ፣ ጠጪ እና ጓደኛ የሌለው ሰው ነበረ። ነገር ግን ረቂቅ በህይወቱ በነበራት ተጽዕኖ ምክንያት መሳይ መጠጥ እየተወ እና እራሱን እያስተካከለ መጥቷል። መሳይ ምንም ያህል ጥረት ቢያደርግም ግን አስቴር ህይወቱን ለማበላሸት ያደረገችው ጥረት ተሳክቷል። መሳይ አሁን የልጅ አባት እና የበሉ ባል ነው።

Yerekik menged S1
yerekik menged poll 7

መሳይ የአስቴርን ድርጊት የሚረሳው ይመስላችኋል?

Click here to make your selection
አዎ ይቅር ይላታል
አይ ይበቀላታል

አስቴር

አስቴር ከረቂቅ ጣልቃ ገብነት በፊትም ህይወቷ ምን መምሰል እንዳለበት ስላ ልጇ ኒና እቅዷን እንድትከተል አድርጋለች። እስከመጨረሻው እቅዷን ለመፈጸም እና የአቶ ገዛህኝን ሀብት የእራሷ ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት አላቆመችም። እንድ ደጋፊዋ ልጇን እራሱ አጥታ የምታደርገውን ማቆም አልፈለገችም፣ ይልቅስ ለአቶ ገዛህኝ የውሸት ለቅሶ አዘጋጅታለች።

Yerekik menged S1
yerekik menged poll 8

አስቴር እቅዷን በመጨረሻ ታሳካለች?

Click here to make your selection
አዎ ታሳካለች
ኒና ታስቆማታለች
አዎ ታሳካለች
ኒና ታስቆማታለች

ረቂቅ በዚህ ሁሉ ሰው ህይወት ላይ ሆን ብላም እና ሳታስበው ትልቅ ተጽዕኖ አሳድራበታለች።

Yerekik menged S1
yerekik menged poll 9

ረቂቅ ፍትህ ታገኛለች?

Click here to make your selection
አዎ ታገኛለች
አይ አታገኝም

ለእነዚህ ግምቶች መልሱን በመጨረሻው የረቂቅ መንገድ ክፍል በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ያግኙ!