Logo
Tilla Slim Billboard 1600x600 copy
channel logo

Tilla

465DramaPG13

አቦል ቲቪ አንደኛ አመቱን ሊያከብር ነው!

ዜና
01 ማርች 2022
ከአቦል ቲቪ አዳዲስ ድራማዎችን ይጠብቁ!

በአቦል ቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ልዩ ልዩ ታሪኮችን ለውድ ተመልካቾቻችን ይዘን ከቀረብን አንድ አመት ሞልቶናል! ባለፈው አንድ አመት ውስጥ በኢትዮጵያዊያ ለኢትዮጵያን የተዘጋጁ አስቂኝ፣ ልብ አንጠልጣይ እና አስደናቂ ታሪኮችን ስናቀርብ ቆይተናል። አሁን ደግሞ ልደታችንን ከውድ ተመልካቾቻችን ጋር ለማክበር አዳዲስ ታሪኮችን ይዘን እንቀርባለን። በአቦል ቲቪ በጉጉት ስለሚጠበቁ ድራማዎች ለማወቅ ይሄንን ይመልከቱ።

በጊዜ ቤት

አዲሱ የአቦል ቲቪ ሲትኮም አንድ ዮሴፍ(ጆሲ) የተባለ ወጣት ባላሰበው መንገድ ከሚመቸው እና ከለመደው የተቀናጣ የከተማ ህይወት በአሳዳጊዎቹ ውሳኔ ወጥቶ ወደ ትንሽዋ የገጠር መንደር የጋሽ መልካሙ ቤት እንዲኖር ይገደዳል። ከ28 ዓመት የልደት ቀኑ ጀምሮ ካደገበት የከተማ አኗኗር እና ባህል ተቃራኒ የሆነውን የገጠር ህይወት መኖር ይጀምራል። ይህ አስቂኝ ድራማ በአቦል ቲቪ ቻናል 146 ረቡዕ የካቲት 23,2014 ከምሽቱ 1:30 ይጀምራል!

ሁለት ጉልቻ

በኩሬ ከሶስት ሴቶች ጋር በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ያለ ሰው ነው። በዚህ ጊዜ ላይ፣ በአጋጣሚ ሦስቱ ሴቶች በአንድ ዝግጅት ላይ ሲገናኙ ያልጠበቁት ጓደኝነት ይጀምሩና አብረው የጋራ ችግራቸውን ለመወጣት ይሞክራሉ። የሁለት ጉልቻ አስገራሚ ታሪክ ዓርብ የካቲት 25 ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ይቀርባል።

ጥላ

ጫካ ምንም ገንዘብ የሌለውና ከአዲስዋ ሚስቱ ጋር በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚኖር ሰው ነው። ከዕለታት አንድ ቀን ግን ቤቱ ያሳደራቸው ሽማግሌ፤ ላሜ ቦራ የተባለችው ላም ከድህነት እንደምታወጣውነግረውትና መርቀውት ይሄዳሉ፡፡ ሆኖም ይህ ምርቃት በድህነት በወደቀው ቤቱ ላይ ሌላ የማይፈለግትኩረትና መከራ ያመጣል። ጫካም ያንን ትንቢት ለማስፈጸምና ከድህነት ለመውጣት የወሰደው ውሳኔ ቀጣይ ህይወቱን በሃብት ብቻ ሳይሆን በውጣ ውረድ የተሞላ ያደርግበታል፡፡ አሁን ብቸኛው ተስፋውከመጀመሪያ ሚስቱ በተወለደችው በሴት ልጁ በፍኖት ላይ ነው። ጥላ ድራማ ስለፍቅር አዲስ ሀሳብ ይዞ ሰኞ የካቲት 28 ከምሽቱ 2:30 በአቦል ቲቪ ይጀምራል።

የባስሊቆስ እንባ

ሁሉም ሰው እርስ በራስ የሚተዋወቅበት ዳባት የተባለ ትንሽ ከተማ አለ። ብርሃን የተባለች አንዲት ወጣት ሴት አዲስ አመትን ከቤተሰቧ እና ለብዙ አመታት አግኝታው የማታውቀው የልጅነት ፍቅረኛዋ ጋር ለማሳለፍ፣ ከኮሌጅ ትመጣለች። ይህ አስደሳች ታሪክ ብርሃን ከልጅነት ፍቅረኛዋ ጋር ለመታረቅ ስትሞክር የምታሳልፋቸው ልዪ ልዪ ጊዜያት እና አስገራሚ አጋጣሚዎችን ያቀርባል። ይሄን አስደሳች የፍቅር ታሪክ ማክሰኞ መጋቢት 21 ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ መከታተል ይችላሉ።

ከእነዚህ አዳዲስ አቅርቦቶች የትኛውን ድራማ በጉጉት ይጠብቃሉ? መልስዎን ኮመንት በማድረግ ያሳውቁን!

ውድ ተመልካቾቻችንን ባለፈው አመት ውስጥ ለአቦል ቲቪ ላደረጋችሁት ድጋፋ ማመስገን እንፈልጋለን

የበለጠ አስደሳች ጊዜያትን ከአቦል ቲቪ ጋር ለማሳለፍ ቻናሉን በዲኤስቲቪ ቻናል 146 መከታተል ይቀጥሉ!