ምስኪኖቹ ድራማ የአንድ ምራት ኤደን እና ሙልዬ መስተጋብሮችን የሚያቀርብ ድራማ ነው። ሙልዬ የምትወደው ልጇን ፍቅር ላለማጣት ስትጥር፣ ኤዱ ደግሞ የምትወደው ባሏን ጊዜ ከእናቱ በላይ ለመሻማት ትሞከራለች። በዚህ ማሃል እያሱ እናቱን እና ሚስቱን የሚያስደስት ነገሮችን ለማግኘት ይሞክራል። በመጀመሪያው ምዕራፍ ኤዱ ተምራ ወደ እናቷ ቤት ተመልሳ ነበር፣ የምዕራፍ 2 የመጀመሪያው ክፍል ደግሞ እዩ፤ ኤዱን ወደ ቤት ለማስመለስ የሚያደርገውን ጥረት አይተናል።
ከዚህ ክፍል ውስጥ እነዚህ ሶስት ክስተቶች አዝናተውናል እናም እርስዎን ያዝናናሉ ብለን እናምናለን።
- ኤደን ወደ ቤት ለመመለስ በሽማግሌ መለመን መፈለጓ።
ኤደን፣ በሙልዬ ቤት እያለች ብዙ አስገራሚ ነገሮችን አድርጋ ነበር። እንዳረገዘች ሙልዬን ማሳመን፣ እዩን ለማስቀናት መሞከር እና ምግብ ማብሰል ሳትችል እንግዳ ለእራት መጥራት እና ከዚህም የተለዩ ሌሎች ድርጊቶችን ፈጽማለች። ስለዚህም ከትዳሯ እረፍት መውሰዷ እና እዩ ስለ ናፈቃት ሽማግሌ እንዲልክ ማስደረጓ ለኤደን አዲስ ባህሪ አይደለም። ኤደን ከሙልዬ ጋር የገጠመችውን ትግል የሚከፈለውን ዋጋ ከፍላ ማሸነፍ እንደምትሞክር አይተናል።
- እዩ እናቱን አታልሎ ሽማግሌ መላኩ!
እዩ እናቱን እና ሚስቱን በጣም ቢወዳቸውም ሁለቱን አንድ አስማምቶ ደስ ማሰኘት አልቻልም። ስለዚህ ኤዱን እየናፈቀ ሳለ እሷን ወደ ቤት ለመመለስ ሽማግሌ መላክ እንዳለበት ሲረዳ ወድያውኑ ለማስፈጸም ነው የሞከረው። ነገር ግን ይሄንን ሀሳብ ሙልዬ ስለምትቃወመው በድብቅ ሽማግሌዎችን ፈልጎ ሙልዬ ጋር እንዲቀርቡ አድርጓል። እዩ ሚስቱን ወደ ቤት ለመመለስ ምንም ከማድረግ ወደኋላ እንደማይል አሳይቶናል።
- ሙልዬ ሽምግልና ለመቅረብ ተገደደች!
ሙልዬ፣ በእዩ እቅድ ተሸውዳ ኤደን ጋር ሽምግልና ለመቅረብ ተገዳለች። በኤዱ ፍላጎት ሳትስማማ ለመቅረብ የተገደደችው ሙልዬ ሽምግልናው ከባድ እንዲሆን ታደርገዋለች። ከኤዱ ጋር ያላትን ግጥሚያ ለማሸነፍ የምትችለውን ሁሉ እንደምትሞክር ግልጽ አድርጋለች።
የዚህ ቤተሰብ ድራማ ታይቶ የማይጠገብ አስቂኝ ጊዜ ነው። እርስዎ በዚህ ምዕራፍ ምን አይነት ክስተቶችን ይጠብቃሉ? በማህበራዊ ሚድያ ያሳውቁን!
ምስኪኖቹ ድራማ ዘወትር ሰኞ ከምሽቱ 3፡00 በአቦል ቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ!