የምስኪኖቹ ታሪክ በአማት እና ምራት ሙልዬ እና ኤደን ያጠነጠነ ነው። ሁለቱ ለእዩ ፍቅር እና ጊዜ በአስቂኝ መንገድ ሲወዳደሩ እናያለን። በዚህ ታሪካዊ ቤተሰብ መሀል የሚፈጠረው አለመግባባት አስቂኝ ነው።
ሶስቱ በጣም አስቂኝ የምንላቸው ጊዜያት እነዚህ ናቸው፦
- ኤዱ የቤተሰብ አባል እንዳልሆነች ይሰማታል።
ሙልዬ ኤዱን እቤት በመተው የቤተሰብ ጉዳይ ማስፈጸም ትፈልጋለች። ነገር ግን እዩ እና ሙልዬ ድብብቆሽ ማብዛታቸው ኤዱን ያጠራጥራታል። ኤዱ እውነቱን ከእዩ ለመስማት ያደረገችው ጥረት በጣም አስቂኝ ነበር።
እዩ እውነቱን ሙልዬ በምትፈልገው መንገድ ይደብቃል ወይስ ለኤዱ ይነግራታል?
የእዩን ምርጫ ይመልከቱ:
- እዩ፣ ኤዱን በሌላ ሴት ስም ይጠራታል።
ኤዱን የሚያስቀናት ነገር የእዩ የድሮ ፍቅረኛ ሊሊ ስትነሳ ነው። እዩ በስህተት ኤዱን በድሮ ፍቅረኛው ስም ሲጠራ በመሀላቸው ትልቅ ችግር ይፈጠራል። እዩ በኤደን መልስ ሲጠራጠር ኤዱ ደግሞ እራሷን ለመቆጣጠር ትሞክራለች፣ ይህ አዝናኝ ጊዜያትን ይፈጥራል።
የኤዱን መልስ ይመልከቱ።
- ኤዱ የሙልዬ አስታራቂ ሆነች።
ኤዱ ሙልዬ ከተጣላቻት ጓደኛዋ ጋር በመገኘቷ ቤት ውስጥ ትልቅ ጸብ ይፈጠራል። ሙልዬ ኤዱ ከጠላቷ ጋር ጓደኝነት ጀምራለች ብላ በማመኗ ከኤዱ ጋር ትጣላለች። ኤዱ ንጹህ መሆኗን ለማስመስከር የምታደርገውን ጥረት በጣም አስቂኝ ነበር።
ይበልጥ ይመልከቱ፡
እነዚህ ሶስት ጊዜያት በምዕራፍ 2 ላይ አዝናንተውን ነበር። እርስዎ በጣም ያስደሰትዎት ጊዜ ምን ነበር? በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ኮሜንት በማድረግ ያሳውቁን!