Logo
channel logo

Hamza

465DramaPG13

ውስብስብ የፍቅር ታሪክ፣ ያልተጠበቀ በደል እና ልብ አንጠልጣይ ድራማ በሀምዛ

ዜና
26 ኤፕሪል 2024
ከሀምዛ ድራማ የወደድናቸው ልብ አንጠልጣይ ታሪኮች እና ገጸ ባህሪያት።
hamza s1 article 1

የአቦል ቴቪ አዲሱ አቅርቦት ሀምዛ" ውስብስብ የፍቅር ታሪክ፣ ክሕደት እና ልብ አንጠልጣይ ድራማ ይዞ የሚቀርብ አስደና ድራማ ነው። ሀምዛ የተሰኘው ድራማ ከተለያ ቦታ የመጡ የአለም እና ዳንኜን የፍቅር ታሪክ እና ሊያለያያቸው የተነሳ ቤተሰብን ተግዳሮት ያሳየናል።

ውስብስብ የፍቅር ታሪክ

የሚታወቀው ውስብስብ የፍቅር ታሪክ የራሱ የሆነ ተግዳሮቶች በ “ሀምዛ" ውስጥ ማዕከላዊ ደረጃን ይይዛል። አለም እና ዳኜ በደስታ በፍቅር ላይ ሆነው ለቀለበት ቀናቸው እየተዘጋጁ ነው፣ ግን መኳንንት የተባለ ሀብታም ወጣት ፍቅራቸውን የሚያደናቅፍ ሌላ እቅድ አሉት። ምንም እንኳን እሷ የእርሱን ፍቅር የማታውቅ ብትሆንም፣ መኳንንት የአለምን ልብ ለማሸነፍ ቆርጧል። የመኳንንት እቅድ ተሳክቶ፣ የዳኜ እና የአለም የቀለበት ስነ ስርዓት በዳኜ ድንገት መታሰር ይስተጓጎላል ይህም ተመልካቾች በመኳንንትን ድርጊት ሥነ ምግባር ጥያቄ እንዲያነሱ ያደርጋቸዋል።

ያልተጠበቀ በደል

ባልተጠበቀ ክስተት፣ መኳንንት ለአለም ያለው ፍቅር ሲጋለጥ ለመክሊት የክህደት እና የልብ ሕመም መንስኤ ሆኗል። የመኳንንት ሚስጥራዊ ፍቅረኛው መክሊት፣ የቤተሰቡ ቤት ውስጥ አገልጋይ እና የአለም የቅርብ ጓደኛ ስትሆን መኳንንት በድንገት የአለምን ግብዣ ለማስቆም በመወሰኑ ትደነግጣለች። መኳንንት ስለእርሱ ያላትን ጥሩ ልብ ወደጎገን በመተው ሌላ ሰው ለማግባት ሲጥር ስላየችው ከሷ በስተቀር ማንንም እንዳያገባ ለመከላከል ቃል ትገባለች በዚህ ምክንያት አሁን ባለው የግንኙነ ሰንሰለት ላይ ሌላ ውስብስብ ድር ይጨምራል።

Hamza s1
hamza s1 poll 1

መክሊት፡ መኳነንት እንዳያገባ ለማድረግ መወሰኗ ትክክል ነው?

አዎ መዋሸት አልነበረበትም0%
አይ መተው አለባት0%

ልብ አንጠልጣይ ድራማ

አደጋው እየጨመረ በሄደ ቁጥር ድራማው እየጠነከረ ይሄዳል። መኳንንት ለአለም ስላለው ፍቅር እናቱ ከባድ እርምጃዎችን እንዲወስድ ታነሳሳዋለች። ስለዚህም መኳንንት ዳንጌን ለመጋፈጥ እና ሕይወቱን ለማጥፋት ይነሣል ነገር ግን የዳኜ ታማኝ ጓደኛ በሆነው በክንዴ ይጠቃል። መኳንንት በተሳሳተ መንገድ ዳኜን አጥቂው እሱ ነው ብሎ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ያደርጓል በዚህ የተነሳ የቀለበት ስነ ስርዓቱን ያበላሻል።

Hamza s1
hamza s1 poll 2

ክንዴ መኳንንትን አጥቅቶ ዳኜ ሲታሰር ዝም ማለቱ ትክክል ነው?

አዎ እራሱን መጠበቅ አለበት0%
አይ መናገር ነበረበት0%

“ሀምዛ" የተሰኘው ልብ አንጠልጣይ ድራማ በሚያስደንቅ ገጸ-ባህሪያቱ እና በሚያስደስት ታሪኩ ተከስቷል። አዲሱን የሀምዛ ድራማ አቅርቦቶችን ዘወትር ማክሰኞ ከምሽቱ 3 ሰዓት በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 እንዳያመልጥዎ! በ #MyDStv አፕ አሁን አገልግሎቱን ያስቀጥሉ: https://tinyurl.com/yc8p3xvd እና በ DStv Stream App የሚወዱትን የአቦል ቲቪ ድራማዎች ይመልከቱ፡ http://tinyurl.com/bdh2j9ed