Logo
Gojwachin S1 Slim Billboard Desktop
channel logo

Gojwachin

466Reality13

በኢትዮጵያ የመጀመርያ የሠርግ ሪያሊቲ ሾው አሰራር - ጎጇችን

ዜና
23 ኤፕሪል 2021
መጋቢት 3 በአቦል ቲቪ የተጀመረው የኢትዮጵያ ሠርግ ሪያሊቲ ቲቪ ሾው፣ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የሰዉን ትኩረት ስቧል።

ጎጇችን በኢትዮጵያውያን የሠርግ ስነስራአት ላይ የተመሰረተ ሪያሊቲ ቲቪ ነው። ኢትዮጵያዊ ጥንዶች ለሰርጋቸው ቀን ሲዘጋጁና በመጨረሻም ሰርጋቸው ምን እንደሚመስል እናያለን። ጥንዶቹን በሰርጋቸው እለት በመከተል ውጣ ውረዳቸውን እና የተለያየ ባህላዊ የሰርግ ስነስርዓትም እናያለን።

ግን እንደ ጎጇችን አይነት ሪያሊቲ ቲቪ ለመስራት ምን ምን አይነት ነገሮች መካተት አለባቸው? ከዚህ ልዩ ትርኢት ዳይሬክተር፣ አቤኔዘር መሰረት፣ ጋር በጎጇችን ቀረጻ ጊዜ ምን እንዳጋጠመው እና ምን እንደተማረበት ለመረዳት ጥያቄና መልስ አድርገናል።

በዚህ ሪያሊቲ ቲቪ ሾው ላይ በመስራትህ አስደሳች የምትለው ነገር ምንድን ነው?

እንደዳይሬክተር ተደስቼበታለው የምለው ነገር ቢኖር ከተለያዩ የኢትዮጵያ ባህሎች ጋር መስራቴ ነው። በሰዎች አእምሮ ውስጥ የተቀረፀውን የኢትዮጵያ ባህል በሰፊው ለማየት አስችሎኛል። በተጨማሪም፣ በስራቸው በጣም ጎበዝ የሚባሉ ሰዎችን ነው ያሰባሰብነው ግን አንዳቸው ያንዳቸውን የስራ ችሎታ ምን እንደሚያክል ገና አያውቁም ነበር። አረጋውያንን አግኝተን የአገር በቀል እውቀታቸውን እና ጥበባቸውን መካፈል መቻላችን በጣም ደስ ይል ነበር ፣ እኚህ ትሁት ሰዎች እኛን እቤታቸው ወስደው አልጋና ምግባቸውን አጋርተውን ነበር፣ ይህ ለከተማ ሰው አዲስ ነገር ነበር።

ወደ ሰዎች ሠርግ መጋበዝ ለኛ ትልቅ ነገር ነበር ፣ በዚህ ጉዞ ላይ ብዙ ነገሮችን መማር ችለናል። ስለራሳችን ባህል እንድንማር ዲኤስቲቪ እድሉን ስለሰጠን በጣም ነው የማመሰግነው። ተመልካቾቻችን ልክ እደኛ በእነዚህ ሰርጎች ሊደሰቱባቸው እና ሊማሩባቸው ይችላሉ ብዬ አምናለው።

እስካሁን በጣም የሳበህን ቦታ ግለጽልን?

ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ቦታዎች ተጉዤ አውቃለሁ፣ ግን በእነዚህ ጊዜያት እኔ እንደቱሪስት የሄድኩባቸው ቦታዎች የቱሪስት መስህቦች ወዳሉበት ቦታ ብቻ ነበር። ስለዚህ ወደነዚህ ቦታዎች ተመልሼ ስሄድ ቦታው ተመሳሳይ ቢሆንም ያጋጠሙኝ ነገሮች ይለዩ ነበር። ይህ የሆነበት ምክንያት ከአከባቢው ማህበረሰቦች ጋር እውነተኛ ግንኙነት የመፍጠር እድል ስለነበረኝ ነው። እናም በጣም የገረመኝ ቦታ በአፋር ክልል ሰመራ ውስጥ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ፣ አብዛኛው ቡድኑ እና እኔ ስለዚህ አካባቢ ትክክለኛ ቅድመ ግንዛቤ ስላልነበረን ነው።

አግብተሃል? ብትችል ኖሮ ሠርግህን እንዴት ታከብረው ነበር?

ገና አላገባሁም። በቅርቡ ለማግባት ካቀድኩ ግን በዚህ ፕሮጀክት ላይ መሥራት በራሴ ትኩረት ማድረግ ያለብኝን ዋና ዋና ቦታዎች እዳውቅ እረድቶኛል። ለእኔ፣ ማንኛውም ሠርግ ማተኮር አለበት ብዬ የማምነው ከሠርጉ በኋላ ስሚኖረው የጥንዶቹ ህይወት ነው። ያ ማለት የዝግጅት እንቅስቃሴዎች እኛ ባለን አቅም ላይ የተገደቡ መሆን አለባቸው ማለት ነው። ከዛም አልፎ በሠርጌ ውስጥ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፉ አንድ አንድ ባህላዊ ነገሮች እንዲኖሩ እመኛለሁ። ግን ብዙ ጊዜ ሴቶች እንደሚፈልጉት ሠርግ ዝግጅት እንዲካሄድ ይፈልጋሉ፣ ስለዚህ እሷ የምትፈልገውን ማድረጌ አይቀርም።

ስባህላዊ የሰርግ ዝግጅቶች ምን ያኮራሃል?

ከተለያዩ የኑሮ ዘርፎች የመጡ እነዚህ ሰርጎችን መዘገብ ትልቅ ክብር ነው። በሀገራችን ባሉ ውብ ክብረ በዓላት ተደምሜያለሁ። በጣም ያኮራኝ ነገር ቢኖር የሃገሪቷን ባህል አሁን ካለው የሠርግ ስርአት ጋር አዋህደን ማክበር መቻላቸን ነው። አሁን በመላው ዓለም ባጋራነው ባህላዊ ሠርጎች ምክንያት ኢትዮጵያዊ በመሆኔ የበለጠ ኩራት ይሰማኛል።

ጎጇችን በአቦል ቲቪ ዲኤስቲቪ ቻናል 146 ላይ ዓርብ ከምሽቱ 2:30 እንዳያመልጥዎ!