channel logo
Dinknesh S1

ዲንቅ ነሽ አዲሱ የአቦል ቲቪ ድንቅ ድራማ

ዜና
21 ጃንዩወሪ 2025
የአቦል ቲቪ ድንቅ አዲስ ድራማ ድንቅነሽ አርብ ጥር 9 ይጀምራል!
Dinknesh S1 article

ድንቅነሽ ውብዓለም የተባለች አንዲት በችግር የተሞላ ህይወት ያሳለፈችን ሴት ህይወት ታሪክ በልዩ መንገድ ይተርካል። በድንቅነሽ የሚቀርቡትን ገጸ ባህሪያት እንተዋወቃቸው።

ውብዓለም

መልከ መልካም ባለመሆኗ ከልጅነቷ ብዙ ተገፍታለች። ቲያትር ቤት ውስጥ በፅዳት ስራ የመስራት እድሉን ስታገኝ ህይወቷ ወደ አዲስ ምዕራፍ ይሸጋገራል።

ቤሪ

ገና በወጣትነቷ የስኬት ጫፍ ላይ የደረሰች ተዋናይት ናት። አሁን ግን አዲስ ተፎካካሪ፣ የነበራትን ተወዳጅነት ለመቀማት እየሞከረች ነው።

እምዬ

ቆንጆና ደስተኛ የትዳር ህይወት የነበራት፣ የልጇ አባት በድንገት ሲሰወር ሌላ ባል ታገባለች። ይህም የእሷን እና የልጇን ህይወት ወደ ምስቅልቅል ይቀይረዋል።

አበጋዝ

ተወዳጁ የቲያትር አዘጋጅ አበጋዝ “ድንቅነሽ” የተሰኘ መጽሐፍ በቲያትር ለማዘጋጀት ተወዳጇን አርቲስት ቤሪን በመምረጡ ከፍተኛ ተቃውሞ ይገጥመዋል።

እነዚህን ልዩ ልዩ ገጸ ባህሪያት በድንቅነሽ ድራማ ለማየት በጉጉት እየተጠባበቅን ነው! ድንቅ ነሽ አርብ ጥር 9 ከምሽቱ 2፡00 በአቦል ቲቪ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይጀምራል!