Logo
dagmawi s1
channel logo

Dagimawi

465DramaPG13

ጠበቃ ለመሆን አስፈላጊ ባህሪያት አልዎት? ጥያቄዎችን በመመለስ ይወቁ!

ዜና
16 ኖቬምበር 2023
ጠበቃ ለመሆን ምን አይነት ባህሪያት ያስፈልጋሉ?
what it takes to become a lawyer dagmawi article

“ዳግማዊ” የተሰኘውና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው ተከታታይ ድራማ ዘወትር ሰኞ ከምሸቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በአቦል ቴሌቪዥን የሚተላለፍ ይሆናል፡፡ “ዳግማዊ” በአንድ ወቅት በሀዋሳ ከተማ አጋጥሞ በነበረ እውነተኛ ታሪክ ላይ በተጻፈው ዳግማዊ መጽሐፍ ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ ሲሆን ስለ ተጨባጭ ፍትህ ሲባል አደጋን ስለተጋፈጠው ወጣት ጠበቃና ጓደኛው የሚተርክ ነው፡፡ የእነርሱ አሳዛኝ፣ ነገር ግን ደፋር ጉዟቸው በመማር ልምድ፣ በፈተናዎች እና አስደንጋጭ ድርጊቶች የተሞላ ሲሆን ይህ እውነተኛ ታሪክም ተመልካቾችን እንደሚያስደንቅ ጥርጥር የለውም። ዳግማዊ የሞራል ልዕልና፣ የወጣትነት እውነትን ፍለጋ ውስብስብ ጉዳዮችን ይዳስሳል። የዚህን አስደናቂ ድራማ ጅማሪ በጉጉት እየጠበቅን ነው፣ እስከዛም እነዚህን አዝናኝ ጥያቄዎች ለእርስዎ አዘጋጅተናል!

dagmawi s1
dagmawi poll 1

አለመግባባት ሲፈጠር ምን ያደርጋሉ?

እከራከራለሁ 23%
ስለ ርእሱ የማውቀውን በማቅረብ አግባባለሁ77%
dagmawi s1
dagmawi poll 2

ቤተሰብ እና ጓደኛዎ ምን አይነት ባህሪ አለዎት ይላሉ?

ተግባቢ75%
ተከራካሪ25%
dagmawi s1
dagmawi poll 3

የሰዎች መብት ሲነካ ምን አይነት አስተያየት አለዎት?

የኔ መብት እስካልተነካ ድረስ አያገባኝም10%
ትክክል ስላልሆነ እቃወማለሁ90%
dagmawi s1
dagmawi poll 4

ምን አይነት የፊልም ይዘት መመልከት ይወዳሉ?

ፍቅር ፊልም30%
አክሽን ፊልም70%
dagmawi s1
dagmawi poll 5

አንድ ሰው ወንጀል ሲፈጽም ካጋጠምዎት ምንድን ያደርጋሉ?

ስለማይመለከተኝ ምንም አላደርግም0%
ለፖሊስ አመለክታለሁ100%

በጣም ጥሩ! መልስዎ ሁለተኛው ምርጫ ከነበረ ጠበቃ ለመሆን አስፈላጊ ባህሪ አለዎት ብለን እናምናለን። የመጀመሪያዎችን ምርጫዎች ከመረጡ ምን አልባት ጠበቃ ላይሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን እንዳያዝኑ አዲሱ የአቦል ቲቪ ድራማ #ዳግማዊ በመመልከት ጥብቅና ለእርስዎ የሚሆን ከሆነ መወሰን ይችላሉ።

#ዳግማዊ ሰኞ ኅዳር 10 ከምሽቱ 3፡00 በ #አቦልቲቪ ፣ ዲኤስቲቪ ቻናል 465 ይጀምራል!